አቶ ጌታቸው ረዳ ምርጫ ቦርድ ህወሓትን "በልዩ ሁኔታ" በፓርቲነት መመዝገቡን ተቃወሙ
አቶ ጌታቸው ለምርጫ ቦርድ የቀረበው የህወሓት ማመልከቻ ማዕከላዊ ኮሚቴው የማያውቀው ነው ብለዋል
ምርጫ ቦርድ የሰጠው ምዝገባ በተጭበረበረ ማስረጃ በመሆኑ መልሶ እንዲመረምረው ጠይቀዋል
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንትና የህወሓት ምክትል ሊቀ መንበር አቶ ጌታቸው ረዳ ምርጫ ቦርድ ህወሓትን "በልዩ ሁኔታ" በፓርቲነት መመዝገቡን ተቃወሙ።
ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ትናንት ነሐሴ 03 ቀን 2016ዓ.ም ለህወሓት በልዩ ሁኔታ የምዝገባና የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት መስጠቱን ይታወቃል።
ቦርዱ ይህንን በማስመልከት በተመሳሳይ ቀን በሰጠው መግለጫ በተራ ቁጥር 2 ደግሞ ህወሓት የፓርትው ኃላፊዎች ስምና ፊርማ የያዘ ሰነድ ማቅረቡን ይፋ አድርጓል።
ይህንን ተከትሎ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንትና የህወሓት ምክትል ሊቀ መንበር አቶ ጌታቸው ረዳ ለምርጫ ቦርድ በጻፉት ደብዳቤ ቀርቧል የተባለውን የምዝገባ ጥያቄ ህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ የማያውቀው ነው ሲሉ ገልጸዋል።
አቶ ጌታው አክለውም “እኛ ደግሞ ለዚሁ ምዝገባ ብለን የፈረምነው ምንም ዓይነት ሰነድ ሳይኖር ግለሰዎች ብቡድን ተደራጅተው ከድርጅቱ አሰራር ውጭ የፈፀሙት ያልተገባ ተግባር መሆኑን ማሳወቅ እንወዳለን” ብለዋል።
“ድርጊት እኛ የማናውቀው እና በድርጅቱ ስም ምዝገባ የጠየቁ ግለሰዎችም እኛን ሳያስፈቅዱ የፈፀሙት መሆኑን እየገለፅን” ብለዋል አቶ ጌታቸው ለምርጫ ቦርድ በጻፉት ደብዳቤ።
“ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለነዝህ ግለሰቦች የሰጠው ምዝገባ በተጭበረበረ ማስረጃ መሰረት የተሰጠ በመሆኑ መልሶ እንዲመረምረው እንጠይቃለን” ብለዋል።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በትናንትናው እለት ባወጣው መግለጫ ህወሓት ጠየቀው ህጋዊ ሰውነቱ እንዲመለስ ያቀረበው ጥያቄ ውድቅ መሆኑን እና በልዩ ሁኔታ እንዲመዘገብ ውሳኔ ማሳለፉን መግለጹ ይታወሳል።
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንትና የህወሓት ምክትል ሊቀ መንበር አቶ ጌታቸው ረዳ ባሳለፍነው ሃሙስ ለህወሓት ሊቀ መንብር ደብረጺዮን ገብረሚካዔል (ዶ/ር) በጻት ደብዳቤ ከህወሓት ድርጅታዊ ጉባዔ ራሳቸውን ማግለላቸውን አስታውቀዋል።
“መሬት ያለው ቅጥ ያጣ እንቅስቃሴ መጨረሻ ላይ ድርጅቱን እና ህዝባችንን ወደ ከፋ አደጋ እንደሚያስገባ ግልጽ እየሆነ ነው” ያሉት አቶ ጌታቸው፤ “አሁን እየተደረገ ስላለው ቅጥ ያጣ እንቅስቃሴ እኔም ሆነ የማዕካለዊ ኮሚቴውአናውቀውም” ሲሉም ገልጸዋል።
አቶ ጌታቸው “ህገ ወጥ” ያሉት ቡድን ማዕካለዊ ኮሚቴው ለምዝገባ ብሎ ያልፈረመበት የተጭበረበረ ሰነድ አያይዞ በአዲሱ አዋጅ መሰረት ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ጥያቄ ስለማቅረቡም በደብዳቤያቸው መግለጻቸው ይታወቃል።
“ይህ አካሄድ ተራ ስህተት ሳይሆን፤ ድርጅቱን ለማፍረስ እና የትግራይ ህዝብን የህልውና ትግል ከንቱ ለማድረግ ሆን ተብሎ እየተሰራ ያለ የጥፋት ቡድን እንቅስቃሴ ነው” ሲሉም ገልጸዋል።
አቶ ጌታቸው እኔን ጨምሮ የየቁጥጥር ኮሚሽን እና በርካታ የድርጀቱ ከፍተኛ አመራር ያነሷቸው ጥያቄዎች በአግባቡ እስኪመለሱ በአንድ ቡድን በተዘጋጀ ጌባዔ ይሁን የድርጅቱ የከፍተኛ አመራሮች ውሳኔ የጣሰ የምዝገባ ሂደት ላይ የማልሳተፍ መሆኔን ለማሳወቅ እወዳለሁ” ብለዋል።