ኢራን አሜሪካ 7 ቢሊዮን ዶላር ካሳ እንድትከፍላት ጠየቀች
የካሳ ክፍያው አሜሪካ በኢራን ላይ በጣለችው ማዕቀብ ምክንያት በመድሃኒት እጥረት ለተጎዱ ዜጎቿ የሚውል ነው ተብሏል
ተመድ ባወጣው ሪፖርት መሰረት ኢራናዊያን በመድሃኒት እጥረት ምክንያት በቀላሉ ይድኑ የነበሩ ህመሞች ወደ ካንሰር እየተቀየረባቸው ይገኛል
ኢራን አሜሪካ 7 ቢሊዮን ዶላር ካሳ እንድትከፍላት ጠየቀች
የዓለማችን ልዕለ ሀያል ሀገር የሆነችው አሜሪካ በኢራን ላይ ለረጅም ዓመታ የዘለቁ ማዕቀቦችን ጥላለች፡፡
የቀድሞው የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ በኢራን ላይ ተጥለው የነበሩ ማዕቀቦች እንዲነሱ ውሳኔ ያሳለፉ ቢሆንም ዶናልድ ትራምፕ ወደ ፕሬዝዳንትነት ሲመጡ ማዕቀቡን አጽንተዋል፡፡
ይህን ተከትሎ ኢራን በተለይም የህክምና ቁሳቁስ እና መድሃኒቶች ከፍተኛ እጥረት እንደገጠማት ተገልጿል፡፡
የኢራን ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት አሜሪካ በኢራን ላይ በጣለችው ማዕቀብ ምክንያት 6 ነጥብ 8 ቢሊዮን ዶላር ካሳ እንድትከፍል ወስኗል፡፡
ፍድርድ ቤቱ ውሳኔውን ያስተላለፈው በመድሃኒት እጥረት ምክንያት ለማይድን ህመም የተጋለጡ የሀገሪቱ ዜጎች ከሶስት ዓመት በፊት በመሰረቱት ክስ መሰረት ነው፡፡
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ባይደን በኔቶ ስብሰባ ወቅት አዲስ ስህተት ሰሩ
የተመድ ባለሙያዎች ቡድን ባወጣው ሪፖርት መሰረት አሜሪካ በኢራን ላይ በጣለቻቸው ማዕቀቦች አማካኝነት በቀላሉ ይድኑ የነበሩ ህመሞች ወደ ካንሰርነት እየተቀየሩ መሆኑን ገልጸው ነበር፡፡
ሪፖርቱን ተከትሎ አሜሪካ የሰብዓዊ ድጋፍ የሚውሉ እንደ ጤና እና መድሃኒት ምርቶችን ከማዕቀቡ ውስጥ ሰርዛለች ተብሏል፡፡
ይሁንና በርካታ ዓለማችን የመድሃኒት አምራች ኩባንያዎች አሁንንም በማዕቀቡ ምክንያት ከኢራን ኩባንያዎች ጋር የመነገድ ፍላጎት እንደሌላቸው አል አረቢያ ዘግቧል፡፡
ኢራን ከሁለት ዓመት በፊት የቀድሞ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን ጨምሮ ማይክ ፖምፒዮ እና ሌሎች ባለስልጣናትን ለመያዝ የእስር ማዘዣ ማውጣቷ ይታወሳል፡፡