ኢራን የእንግሊዝን አምባሳደር ለምን አሰረች?
የእንግሊዝ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቴህራን የሚገኘው የሀገሪቱ አምባሳደር በኢራን መንግስት መታሰሩን ትናንት አረጋግጧል፡፡
አምባሳደሩ ሮብ ማካይር የታሰረው በዩክሬን አውሮፕላን ሟቾች የሀዘን ስነ ስርዓት ላይ መገኘታቸውን ተከትሎ ነው፡፡
አምባሳደሩ ስፍራውን ለቀው ከወጡ በኋላ ወዲያው በአካባቢው ተቃውሞ በመነሳቱ፣ ተቃውሞውን አስተባብረዋል በሚል ተጠርጥረው እንደታሰሩ ነው ከኢራን የተለቀቁ ዘገባዎች ያመለከቱት፡፡
ይሄም ዓለማቀፍ ህግን የተጻረረ ድርጊት እንደሆነ ገልጿል፡፡ በቬና ስምምነት መሰረት ዲፕሎማቶችን ማሰር አይቻልም፡፡
አምባሳደሩ የተለያዩ ዘገባዎች እንደሚያሳዩት ከ1 እስከ 3 ሰዓት ታስሮ ቢለቀቅም እንግሊዝ ድርጊቱን ውጥረት አባባሽ ብላለች፡፡
ከእስራቱ ጋር በተያያዘ የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቴህራን ማብራሪያ እንድትሰጠው ጠይቋል፡፡
ምንጭ፡- ቢቢሲ