ቴህራን እስራኤል አድርሳዋለች የተባለውን ጥቃት "ሰርጎገቦች" የፈጸሙት ነው ስትል አቃለለች
እስራኤል በዛሬው እለት በኢራን ምድር አድርሳዋለች በተባለ የበቀል ጥቃት ፍንዳታ መከሰቱ ተዘግቧል
ክስተቱን ያቃለለችው ኢራን የአጸፋ ምላሽ የመስጠት እቅድ እንደሌላትም አመላክታለች
ቴህራን እስራኤል አድርሳዋለች የተባለውን ጥቃት "ሰርጎገቦች" የፈጸሙት ነው ስትል አቃለለች
እስራኤል በዛሬው እለት በኢራን ምድር አድርሳዋለች በተባለ የበቀል ጥቃት ፍንዳታ መከሰቱ ተዘግቧል።ነገርግን ክስተቱን ያቃለለችው ኢራን የአጸፋ ምላሽ የመስጠት እቅድ እንደሌላትም አመላክታለች።
እስራኤል በኢራን ላይ የድሮን ጥቃት ማድረሷ ተዘገበ
ይህ የኢራን ምላሽ ይቀሰቀሳል ተብሎ የነበረውን ቀጣናዊ ጦርነት የሚያስቀር ይመስላል።
የእስራኤል የተመጠነ ጥቃት እና ኢራን የሰጠችው የዝምታ ምላሽ፣ ኢራን ባለፈው ቅዳሜ በእስራኤል ላይ የሚሳይል እና የድሮን ናዳ ካወረደች ጀምሮ ያለእረፍት ሲሰሩ የነበሩ ዲፕሎማሞች ውጤታማ መሆናቸውን የሚያሳይ መሆኑም ተገልጿል።
የኢራን ሚዲያ እና ባለስልጣናት እንደገለጹት የኢራን አየር መከላከያ ሚሳይል በኢስፋን ከተማ ሰማይ ሶስት ድሮኖችን ሲመታ ፍንዳታዎች ተከስተዋል።
ጥቃቱ እስራኤል አደረሰችው ከማለት ይልቅ "ሰርጎገቦች" የኢራንን የአየር ክልል ጥሰው እንደፈጸሙት የገለጹት ሚዲያዎቹ እና ባለስልጣናት የበቀል እርምጃ መውድን እንደተውት የሚያሳይ ነው ተብሏል።
ሮይተርስ የኢራን ባለስልጣን ጠቅሶ እንደዘገበው ከሆነ በክስቱት እስራኤል የመበቀል እርምጃ የመውሰድ እቅድ የለም።
"ጥቃቱ ከውጭ መሰንዘሩ ገና አልተረጋገጠም። የውጭ ጥቃት አላጋጠመንም፤ መረጃው ከውጭ ይልቅ በሰርጎገቦች የተሰነዘረ ወደሚለው የሚያዘነብል ነው"ብለዋል ባለስልጣኑ።
እስራኤል በዚህ ክስተት ዙሪያ ያለችው የለም።
ነገርግን ከአራት ቀናት በፊት ኢራን ለመጀመሪያ ጊዜ ላደረሰችው ቀጥተኛ ጥቃት ምላሽ እንደምትሰጥ ዝታ ነበር።
ኢራን እና የኢራን ሚዲያዎች ከዛሬው ክስተት ጋር በተያያዘ እስራኤልን ሲያነሱ አልተደመጡም።
የኢራን መንግስት ቴሌቪዥን "ሶስት ድሮኖች በኢስፋን ከተማ ሰማይ ታዩ። የኢራን አየር መከላከያ ሲስተም እነዚህን ድሮኖች አየር ላይ መትቶ አውድሟቸዋል" ሲል ዘግቧል።
ቴሌቪዤኑ ሲየቮሽ ሚሀንዶስት የተባሉ አንድ ከፍተኛ የኢራን ወታራዊ አዛዥን ጠቅሶ እንደዘገበው "አጠራጣሪ ነገሮች" በአየር መከላከያ ሚሳይል ኢላማ ተደርገዋል።
የኢራኑ ፕሬዝደንት ኢብራሂም ራይሲ ከዛሬው ጥቃት በፊት የኢራን ጦር ከእስራኤል የሚሰነዘርን ጥቃት እንደአመጣጡ ለመመከት መዘጋጀቱን እና ምላሽ እንደሚሰጥ ተናግረው ነበር።
ኢራን በትናንትናው እለት እስራኤል የኢራንን ጥቅሞች ኢላማ ከማድረግ መቆጠብ እንዳለባት ለተመድ ተናግራለች።
ኢራን ጥቃቱ በተፈጸመበት ወቅታ ዘግታቸው የነበሩትን የአየር ክልሏን እና አየር መንገዶቿን መልሷ ከፍታለች ተብሏል።