እስራኤል በኢራን ላይ የድሮን ጥቃት ማድረሷ ተዘገበ
አሜሪካ እስራኤል በኢራን ላይ ስላደረሰችው ጥቃት መረጃው ቢኖራትም ጥቃት በማድረስ አልተሳተፈችም ተብሏል
እስራኤል በኢራን ላይ ጥቃት እንዳታደርስ ጫና ሲደረግባት የነበረ ቢሆንም እስራኤል እንደዛተችው ጥቃት ፈጽማለች
እስራኤል በኢራን ላይ የድሮን ጥቃት ማድረሷ ተዘገበ።
እስራኤል በኢራን ላይ ጥቃት ማድረሷን ሮይተርስ ለጉዳዩ ቅርበት አላቸው ያላቸውን ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል።
የኢራን መንግስት መገናኛ ብዙኻን ኢራን በእስራኤል ላይ የድሮን እና የሚሳይል ጥቃት ካደረሰች ከቀናት በኋላ በዛሬው እለት ጠዋት ጦሯ በርካታ ድሮኖችን ማክሸፉን ዘግበዋል።
ሮይተርስ እንደዘገበው አሜሪካ እስራኤል በኢራን ላይ ስላደረሰችው ጥቃት መረጃው ቢኖራትም ጥቃት በማድረስ አልተሳተፈችም።
የኢራኑ ፋርስ ዜና አገልግሎትም በማዕከላዊዋ ኢስፋሃን ከተማ በሚገኘው የጦር ሰፈር አቅራቢያ ሶስት ፍንዳታዎች መሰማታቸውን ዘግቧል።
የኢራን መንግስት ቴሌቪዥን "ሶስት ድሮኖች በኢስፋን ሰማይ ላይ ሲያንዣብቡ ታይተዋል። የአየር መከላከያ ሲስተሙ ኢላማ አስገብቶ አውድሟቸዋል" ብሏል።
ይኸው ቴሌቪዥን ቆየት ብሎ በኢስፋን ያለው ሁኔታ የተረጋጋ መሆኑን እና መሬት ላይ የደረሰ ፍንዳታ እንደሌለለ ዘግቧል።
እስራኤል አድርሳዋልች በተባው ጥቃት ዙሪያ እስካሁን ያለችው ነገር የለም።
በሶሪያ ደማስቆ በሚገኘው ኢምባሲዋ ላይ ለደረሰው ጥቃት እስራኤልን ተጠያቂ ያደረገችው ኢራን፣ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በእስራኤል ላይ ከ300 በላይ ድሮን እና ሚሳይል ማስወንጨፏ ይታወሳል።
እስራኤል ኢራን ከስወነጨፈቻቸው ድሮኖች እና ሚሳይሎች ውስጥ አብዛኞቹን ማክሸፏን እና የደረሰው ጉዳትም አነስተኛ እንደሆነ መግለጿ ይታወሳል።
ይሁን እንጅ እስራኤል ኢራን ያደረሰችው ጥቃት ምላሽ ያስፈልጋዋል የሚል ዛቻ አሰምታ ነበር።
የኢራኑ ፕሬዝደንት ኢብራሂም ራይሲ ከዛሬው ጥቃት በፊት የኢራን ጦር ከእስራኤል የሚሰነዘርን ጥቃት እንደአመጣጡ ለመመከት መዘጋጀቱን እና ምላሽ እንደሚሰጥ ተናግረዋል።
የኢራን እና እስራኤል ግጭት ውስጥ መግባት የእስራኤል እና ሀማስ ግጭትን ወደቀጣናው እንደሚያሰፋው ተንታኞች እየተናገሩ ነው።
ኢራን በትናንትናው እለት እስራኤል የኢራንን ጥቅሞች ኢላማ ከማድረግ መቆጠብ እንዳለባት ለተመድ ተናግራለች።
እስራኤል በኢራን ላይ ጥቃት እንዳታደርስ ጫና ሲደረግባት የነበረ ቢሆንም እስራኤል እንደዛተችው ጥቃት ፈጽማለች።