የቴህራን ድሮኖች በዩክሬኑ ጦርነት ጥቅም ላይ እየዋሉ መሆኑ ተገልጿል
ኢራን “ሻሄድ” እና “አባቢል” የተሰኙትን ጨምሮ በሺዎች የሚቆጠሩ አዳዲስና እጅግ ዘመናዊ ድሮኖችን መታጠቋ ይነገራል።
ከቀናት በፊት በእስራኤል ግዛት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቃት ለመፈጸም ስትሞክርም 170 ድሮኖችን መጠቀሟን አስታውቃለች።
በኢራቅ፣ ሶሪያ፣ ሊባኖስ እና የመን ለምትደግፋቸው ታጣቂዎች ድሮኖችን ታቀርባለች በሚል የምትወቀሰው ቴህራን፥ ለሩሲያ የላከቻቸው ድሮኖችም በዩክሬኑ ጦርነት ጥቅም ላይ መዋላቸው ሲነገር ቆይቷል።
የኢራን ድሮኖች ውጤታማነት በየጊዜው እየተሻሻለ መሄድ እስራኤልን ጨምሮ በቀጠናው ለሚገዳደሯት ሃይሎች ስጋት ቢፈጥሩም ከፍጥነት አንጻር የሚቀራቸው እንዳለ ባለሙያዎች ይገልጻሉ።
የኢራን ዋና ዋና ድሮኖች የትኞቹ ናቸው?
1. “ሻሄድ 136”
እስከ 2 ሺህ 500 ኪሎሜትር በፍጥነት መምዘግዘግ የሚችለው “ሻሄድ - 136” እስራኤል ላይ ጥቃት ማድረስ ይችላል።
2. “አባቢል 2”
“አባቢል- 1” ከ1980 እስከ 1988 በተካሄደው የኢራን እና ኢራቅ ጦርነት ጥቅም ላይ የዋለ ሲሆን፥ “አባቢል - 2” ከ2022 ጀምሮ በታጂኪስታን እየተመረተ ነው ተብሏል።
3. “ሲሞርግ” ወይም “ሻሄድ 171”
ዲዛይኑ በ2011 በኢራን አየር ክልል ከገባው የአሜሪካው “አርኪው-170” የተወሰደው “ሲሞርግ” ወይም “ሻሄድ 171” ከ4 ሺህ 500 ኪሎሜትር በላይ ይምዘገዘጋል።
4. “አራሽ”
“አራሽ” ድሮን በባህር ውስጥ ጥቃት ፈጽሞ ወደመጣበት የሚመለስ ሲሆን፥ ለ9 ስአት ገደማ አየር ላይ እየበረረ መቆየት ይችላል ተብሏል።
5. “ፎትሮስ”
በ2013 የተዋወቀው “ፎትሮስ” አራት ሚሳኤሎች እና ቦምቦች ጭኖ በ2 ሺህ ኪሎሜትር ርቀት የሚገኝ ኢላማን መምታት ይችላል።
6. “ሞሃጄር 6”
ለ12 ስአታት ያለማቋረጥ መብረር ይችላል የተባለው “ሞሃጄር 6” ከ100 እስከ 150 ኪሎግራም የሚመዝኑ የጦር መሳሪያዎችን መሸከም እንደሚችል ይነገራል።