ኢራን 25 ሰዎች እንዲገደሉ አድርጓል ያለችውን ግለሰብ በስቅላት ቀጣች
ኢራን 25 ሰዎች እንዲገደሉ አድርጓል ያለችውን የስዊድን እና ኢራን ጥምር ዜግነት ያለውን ግለሰብ በስቅላት ቀጥታለች
የስዊድን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ስዊድን እና አውሮፖ ህብረት ግድያውን ያወግዛል ብለዋል
ኢራን 25 ሰዎች እንዲገደሉ አድርጓል ያለችውን የስዊድን እና ኢራን ጥምር ዜግነት ያለውን ግለሰብ በስቅላት ቀጥታለች።
ግለሰቡ በፈረንጆቹ 2018 በተካሄደው ወታደራዊ ትርኢት እና በሌሎች ቦታዎች የአረብ ተገንጣይ ቡድንን በመምራት 25 ሰዎች እንዲገደሉ አድርጓል በሚል ጥፋተኛ ተብሎ እንደነበር ሮይተርስ ዘግቧል።
የስዊድን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሀቢብ ፍራጆላህን ቻብ ግድያ በተመለከተ ተቃውሞ ለማሰማት የኢራንን ምክትል አምባሳደር መጥራታቸውን ገልጸዋል።
ቻብ "በመሬት ላይ ያለ ሙሰኛ" በሚል የሞት ፍርድ ተፈርዶበት ነበር።
በነዳጁ ክምችት በሚታወቀው በደቡባዊ ኢራን የምትገኘውን ኪዘርስታን ግዛት እንድትገነጠል የአረብ የትግል እንቅስቃሴን በመደገፍ በፈረንጆቹ 2022 ክስ ቀርቦበት ነበር።
የስዊድን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቶቢያስ ቢልስቶርም ስዊድን ኢራን ይህንን እንዳትፈጽመው ለምነው እንደነበር በብስጭት ተናግረዋል።
የሞት ግጣት ሰብአዊነት የጎደለው ነው ያሉት ሚኒስትሩ ስዊድን እና አውሮፖ ህብረት ግድያውን ያወግዛል ብለዋል።