ፕሬዝዳንት ባደን በሶሪያ የአሜሪካ ጦር ላይ በደረሰ ጥቃት ኢራንን አስጠነቀቁ
ፕሬዝዳንቱ ጦራቸው በኢራን ይደገፋል በተባለው ታጣቂ ቡድኑ ላይ የአጻፋ እርምጃ ከወሰደ በኋላ ነው ቴህራንን ያስጠነቀቁት
ሰሞነኛ ጥቃቶች በአሜሪካና ኢራን መካከል ያለውን ግንኙነች የበለጠ ሊያባብስ ይችላል ተብሏል
ፕሬዝዳንት ባደን በሶሪያ የአሜሪካ ጦር ላይ በደረሰ ጥቃት ኢራንን አስጠነቀቁ።
የአሜሪካ ጦር በሶሪያ ለደረሰው ጥቃት "በኢራን የሚደገፉ ኃይሎች" ላይ አጻፋውን በአየር ጥቃት መልሷል።
ከጥቃቱ በኋላ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አሜሪካውያንን ለመጠበቅ “የኃይል” እርምጃ እንወስዳለን ሲሉ ኢራንን አስጠንቅቀዋል።
ሀሙስ እለት ኢራን ሰራሽ ሰው አልባ አውሮፕላኖች (ድሮኖች) በሶሪያ ባደረሱት ጥቃት አምስት ወታደሮችን ጨምሮ ሰባት ሰዎች ተገድለዋል።
አርብ ዕለት የአሜሪካ ሮኬቶች በምስራቅ ሶሪያ አዳዲስ አካባቢዎችን ኢላማ ማድረጋቸውን ምንጮች ጠቁመዋል።
በሶሪያ የሚገኙና በኢራን ይደገፋሉ የሚባሉት ታጣቂዎች በበኩላቸው ለሚሰነዘርባቸው ተጨማሪ ጥቃት ምላሽ ለመስጠት "ረጅም ክንድ" እንዳላቸው ተናግረዋል።
ሰሞነኛ ጥቃቶች በአሜሪካና ኢራን መካከል ያለውን ግንኙነች የበለጠ ውጥረት ውስጥ ከቶታል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።
ጥቃቶቹ እ.ኤ.አ. በ2015 በኢራን እና በታላላቅ ኃያላን ሀገራት መካከል የተደረሰውን የኒውክሌር ስምምነት ለማደስ የተደረገው ሙከራ መቆም እና ሩሲያ በዩክሬን ጦርነት የኢራንን ሰው አልባ አውሮፕላኖች በመጠቀሟ ምክንያት በዋሽንግተን እና ቴህራን መካከል የነበረውን የሻከረ ግንኙነት የበለጠ ሊያባብስ ይችላል ተብሏል።
በሶሪያ የሰፈረው የአሜሪካ ጦር ለድሮን ጥቃት አዲስ ባይሆንም ሞት ግን ያን ያህል እንደማይደርስ ተነግሯል።
"አትሳሳት አሜሪካ ከኢራን ጋር ግጭት አትፈልግም። ነገር ግን ህዝባችንን ለመጠበቅ በኃይል እርምጃ ለመውሰድ ተዘጋጅተናል” ሲሉ ባይደን በካናዳ ጉብኝት ወቅተሰ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።