ኢራን ከእስራኤሉ ሞሳድ ጋር በመገናኘት የተከሰሱ ግለሰቦችን በሞት ቀጣች
ኢራን ከኑክሌር ፕሮግራሞቿ ጋር በተያያዙ ተቋማቶቿ ላይ በርካታ ጥቃቶችን በማድረስ እና የኑክሌር ተመራማሪን በመግደል እስራኤልን ከሳለች።
ይህ የሞት ቅጣት በዚህ ወር ኢራን ከሞሳድ ጋር በማበር ከሳ በሞት የቀጣቻቸውን ሰዎች ቁጥር ወደ አምስት አድርሶታል ተብሏል
ኢራን ከእስራኤሉ የስላለ ድርጅት ሞሳድ ጋር በመገናኘት የተከሰሱ ግለሰቦችን በሞት ቀጣች።
ኢራን ከእስራኤሉ የሞሳድ የስለላ ድርድት ጋር በማሴር ከሳቸው የነበሩትን አንድ ሴትን ጨምሮ አራት ግለሰቦችን በዛሬው እለት በሞት መቅጣቷን ሮይተርስ ዘግቧል።
ይህ የሞት ቅጣት በዚህ ወር ኢራን ከሞሳድ ጋር በማበር ከሳ በሞት የቀጣቻቸውን ሰዎች ቁጥር ወደ አምስት አድርሶታል ተብሏል።
"ከጽዮናዊው መንግስት ጋር ግንኙነት ያላቸው አራቱ... በህጋዊ ሂደት የሞት ቅጣት ተፈጽሞባቸዋል" ሲል ለፍትህ አካላት ቅርበት ያለው የኢራኑ ሚዛን ዜና አገሌግሎት ዘግቧል።
ግለሰቦቹ በሞሳድ እየተመሩ በኢራን ደህንነት ላይ ኢላማ አድርገው እንደነበር ዘገባው ጠቅሷል።
ኢራን ባለፈው ታህሳስ አጋማሽ በሲስታን ቡልቸስታን ግዛት ከሞሳድ ጋር ግንኙነት ነበረው ያለችውን ግለሰብም በሞት ቀጥታ ነበር።
የሞት ቅጣቱ የተፈጸመው ቫፋ ሀንሬህ፣አራም ኦማሪ፣ራህማን ፖርሃዞ እና ናሳም ናማዚ በተባሉ ግለሰቦች ላይ ነው።
የሞት ቅጣት የተፈጸመባቸው አራቱ ግለሰቦች 10 ሰዎች በተከሰሱበት ወንጀል ዋና ፍርደኛ ሲሆኑ በቀሪዎች ላይ የሞት ቀጣቱ ስለመፈጸሙ አልታወቀም።
የኢራን ብሔራዊ ቴሌቪዥን ኢርና ግለሰቦቹ ከሞሳድ ጋር ነበራቸው ስለተባለው ግንኙነት ሲናዘዙ የሚያሳይ የ10 ደቂቃ ቪዲዮ ፖስት አድርጓል።
ኢራን ከኑክሌር ፕሮግራሞቿ ጋር በተያያዙ ተቋማቶቿ ላይ በርካታ ጥቃቶችን በማድረስ እና የኑክሌር ተመራማሪን በመግደል እስራኤልን ከሳለች። እስራኤል ክሱን አላስተባባለችም፤ ወይም አላረጋገጠችም።
ኢራን ባለፈው ነሐሴ ወር ላይ በመከላከያ ኢንዱስትሪዋ እና ሚሳይል ማምረቻዋ ላይ ከተቀነባበረው ከባድ ጥቃት ደርባ የእስራኤል እጅ አለበት ስትለም ከሳለች።