ኢራን በጄነራሉ ግድያ እጇ አለበት ያለቻትን እስራኤልን እበቀላለሁ ስትል ዛተች
ኢራን ብቀላውን በቀጣናው ባሉ ኤጀንቶቿ ልትፈጽም እንደምትችል ተገልጿል።
የኢራኑ ፕሬዝደንት ኢብራሂም ራይሲም እስራኤልን ዋጋ እንደሚያስከፍሏት ቃል ገብተዋል
ኢራን በጄነራሉ ግድያ እጇ አለበት ያለቻትን እስራኤልን እበቀላለሁ ስትል ዛተች።
ኢራን ታዋቂ ለሆኑት የኢራን ሪቮሉሽነሪ ጋርድ አባል ግድያ እጇ አለበት ያለቻትን እስራኤልን እንደምትቀበል ዝታለች።
የኢራን ሪቮሉሽናሪ ጋርድ ቃል አቀባይ ረመዳን ሸሪፍ በቴሌቪዥን በተላለፈ መግለጫቸው "ሪቮሉሽነሪ ጋርድ ጀነራል ሰይድ ረዛ ሞውሳቪ ለምን እንደተገደሉ እንደሚያውቅ እስራኤል ማወቅ አለባት" ብለዋል።
ቃል አቀባዩ "ተገቢውን ምላሽ እንሰጣለን፤ ብቀላዎቹ በተለያዩ ጊዜዎች እና ቦታዎች የሚፈጸመው ናቸው" ሲሉም ተናግረዋል።
ቃል አቀባዩ እንደገለጹት ለሞውሳቪ ግድያ የሚወሰዱት የብቀላ ተግባራት ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ ይፈጸማሉ።
ኢራን ብቀላውን በቀጣናው ባሉ ኤጀንቶቿ ልትፈጽም እንደምትችል ተገልጿል።
በጄነራል ሞውሳቪ ጉዳይ የተሰጠው ይህ መግለጫ "በሶሪያ የነበረው አንጋፋ የጦር አማካሪያችን ላይ ግድያ" የፈጸመችው እስራኤል ዋጋ ትከፍላለች ብሏል።
የኢራኑ ፕሬዝደንት ኢብራሂም ራይሲም እስራኤልን ዋጋ እንደሚያስከፍሏት ቃል ገብተዋል።
ግድያው "የፍርሃት፣ የድካም እና የአቅም ማጣት" ማሳያ ነው ያሉት ራይሲ እስራኤል "በእርግጠኝነት ዋጋ ትከፍላለች" ሲሉ ተናግረዋል።