ኢምባሲው"ጥያቄው በሀማስ ተቀባይነት በማግኘቱ የተኩስ አቁም ስምምነቱ ከተደረሰ በኋላ 10 የታይ ታጋቾች ተለቀዋል" ብሏል
ኢራን 10 የውጭ ሀገር ታጋቾችን ከሀማስ እጅ ማስለቀቋን ገለጸች።
ኢራን 10 የሚሆኑ የታይ ታጋቾችን ስም ዝርዝር ለፍልጤሙ ቡድን ሀማስ እንዲደርሰው በማድረግ በትናንትናው እለት እንዲለቀቁ ማድረግ መቻሏን ሮይተርስ ዘግቧል።
ኢራን ይህን ያደረገችው የታይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና አፈጉባኤ ጥያቄ በማቅረባቸው መሆኑን በታይላንድ የኢራን ኢምባሲ መግለጹን ዘገባው ጠቅሷል።
ኢምባሲው"ጥያቄው በሀማስ ተቀባይነት በማግኘቱ የተኩስ አቁም ስምምነቱ ከተደረሰ በኋላ 10 የታይ ታጋቾች ተለቀዋል" ብሏል።
የታይ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ የታጋቾችን ዝርዝር ለኳታር፣ ለግብጹ፣ ለእስራኤል፣ ለኢራን እና ለሌሎችም ቀደም ብሎ መስጠታቸውን ገልጸዋል።
ቃል አቀባዩ አክለውም "የተለያዩ አክተሮች በሀማስ ላይ የተለያየ ተጽእኖ ይኖራቸዋል" ብለዋል።
የታይላንድ የሙስሊም ፖለቲከኞች ቡድን ባለፈው ጥቅምት ወደ ኢራን ተጉዘው ከሀማስ መሪዎች ጋር ተነጋግረው ነበር።
የታይላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፖርነፕሪ ባሂዳ ኑካራ ታጋቾቹ በሚለቀቁበት ሁኔታ ከከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በዶሃ እና ኳታር ምክክር አድርገዋል።
የታይ መንግስት 20 የሚሆኑ ዜጎቹ አሁንም ታግተው እንደሚገኙ ተናግሯል።
በእስራኤል 30ሺ የታይ ሰራተኞች ይገኛሉ።