ኢራን የጋዛ ጦርነት መስፋፋት "የማይቀር" ነው ስትል አስጠነቀቀች
እስራኤል በጋዛ በሚገኙ በርካታ ሆስፒታሎች አቅራቢያ እያደረገች ያለው ድብደባ መቀጠሉን የጋዛ ባለስልጣናት እየተናገሩ ነው
እስራኤል፣ ኢራን ሀማስን ትደግፋለች የሚል ክስ በተደጋጋሚ ታቀርባለች
ኢራን የጋዛ ጦርነት መስፋፋት "የማይቀር" ነው ስትል አስጠነቀቀች።
ኢራን የእስራኤል ኃይሎች በሀማስ ላይ እያካሄዱ ባለው ጦርነት እየደረሰ ያለው መጠነሰፊ የንጹሃን ግድያ የግጭቱን መስፋፋት አይቀሬ ያደርገዋል ስትል ገልጻለች።
እስራኤል በጋዛ በሚገኙ በርካታ ሆስፒታሎች አቅራቢያ እያደረገች ያለው ድብደባ መቀጠሉን የጋዛ ባለስልጣናት እየተናገሩ ነው።
የኢራኑ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆሴን አሚር አብዶላሂያን አስተያየት የአሜሪካ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት እና የባህር ኃይሏ ወደ ሜዲትራኒያን መላክ ግጭቱን ከመስፋፋት ያግደዋል ወይስ አያግደውም የሚለውን ስጋት ከፍ አድርጎታል።
አሚር አብዶላሂያን ለኳታር አቻቸው በትናንትናው እለት "በጋዛ በንጹሃን ያለው ጥቃት መጨመር፣ የግጭቱን መስፋፋት አይቀሬ ያደርገዋል" ብለው መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
እስራኤል፣ ኢራን ሀማስን ትደግፋለች የሚል ክስ በተደጋጋሚ ታቀርባለች።
እስራኤል ባለፈው አንድ ወር ውስጥ በጋዛ እያደረገችው ያለው ድብደባ ከፍተኛ የሰብአዊ ቀውስ እንዲፈጠር አድርጓል።
አለምአቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች እና ሀገራት እስራኤል በጋዛ ተኩስ እንድታቆም ቢጠይቁም፣ እስራኤል እና አጋሯ አሜሪካ የተኩስ አቁሙን ሀሳብ አይቀበሉትም።
ተኩስ ማቆም የማይታሰብ መሆኑን የምትገልጸው እስራኤል እርዳታ እንዲደርስ ለማድረግ ግን ለሰአታት ጦርነቱን ጋብ ለማድረግ መስማማቷ ተነግሯል።