ከቃሲም ሱሌማኒ ጋር ልዩ ወዳጅነት የነበራቸው ሚኒስትሩ ቴህራንን ከሪያድ ጋር በማቀራረብም ይታወቃሉ
ኢራን ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲን ጨምሮ ስምንት ሰዎችን ህይወት በቀጠፈው የሄሊኮፕተር አደጋ ብርቱ ዲፕሎማቷን አጥታለች።
ዳምጋን በተባለ ገጠራማ ስፍራ አነስተኛ ገቢ ኬለው ቤተሰብ የተወለዱት ሁሴን አሚር አብዶላሂያን በ60 አመታቸው ህይወታቸው አልፏል።
ከ1980 – 1988 በተካሄደው የኢራንና ኢራቅ ጦርነት ወታደር ሆነው ለሀገራቸው የተዋጉት አብዶላሂያን በውትድርና ማገልገላቸው የውጭ ጉዳይ አተያያቸውን እንደቀየረው ይናገራሉ።
ዲፕሎማቱ በኢራን የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ለረጅም ጊዜ ያገለገሉ ሲሆን በአሜሪካ ከተገደሉት ቃሲም ሱሌማኒ ጋር ወዳጅነታቸው የጠበቀ ነበር።
ሀገራቸው ከአሜሪካ እና ሳኡዲ አረቢያ ጋር ባደረገቻቸው ድርድሮች ትልቅ ድርሻ የነበራቸው ሁሴን አሚር አብዶላሂያን፥ ኢራን በምዕራባውያን እና በእስራኤል ለሚደርስባት ተፅዕኖ ጠንከር ያለ ትችትና ተቃውሞ በማሰማትም ይታወቃሉ።
ስለኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተጨማሪ ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ