ስምንተኛው የኢራን ፕሬዝደንት ራይሲ ሲበሩባት የነበረችው ሄሊኮፕተር ከተራራ ጋር ተጋጭታ በመከስከሷ ህይወታቸው ማለፉን በዛሬው እለት ይፋ ሆኗል
ኢብራሂም ራይሲ ማን ናቸው?
በበሄሊኮፕተር መከስከስ ህይወታቸው ያለፈው ኢብራሂም ራይሲ እሁድ እለት ያደረጉት የሀገረ ውስጥ በረራ አለምን የሚያስጨንቅ የመጨረሻ በረራቸው መሆኑን አያውቁም ነበር።
- በኢራን የሄሊኮፐተር አደጋ የሞቱ የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት እነማን ናቸው?
- በኢራን ፕሬዘደንቱ በማንኛውም ምክንያት ስራቸውን ማከናወን በማይችሉበት ጊዜ ህገመንግስቱ እንደመፍትሄ ያስቀመጣቸው 10 ነጥቦች
ሀሰን ሮሃኒን በመተካት ከነሐሴ 2021 ጀምሮ የሀገሪቱ ስምንተኛው ፕሬዝደንት የሆኑት ራይሲ ሲበሩባት የነበረችው ሄሊኮፕተር ከተራራ ጋር ተጋጭታ በመከስከሷ ህይወታቸው ማለፉን በዛሬው እለት ይፋ ሆኗል።
ኢብራሂም ራይሲ ማን ናቸው?
ራይሲ በናጎን ማሽሀድ በተባለ መንደር ውስጥ በ1960 ተወለዱ። አባታቸው እና የእናታቸው አባት በማሸሀድ የሚታወቁ የሀይማኖት አስተማሪዎች ነበሩ።
ራይሲ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በጃዋዲያህ ትምህርት ቤት ካጠናቀቁ በኋላ በዚሁ ከተማ የሀይማኖት ሰሚናር መከታተል ጀመሩ። የሰሚናሩን የመጀመሪያ ደረጃ ካጠናቀቁ በኋላ 15 አመት ሲሞላቸው በሀይማኖት መምህራን ለመማር ቆም ወደተባለች ከተማ አምርተዋል።
ራይሲ በማሽሀድ ከተማ በነበሩበት ወቅት የኢራኑ የጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ካሚኒ ተማሪ ስለነበሩ ለእሳቸው ቅርቡ ከሆኑት መካከል አንዱ ናቸው።
በሀይማኖት ዘርፍ ባለው ትምህርታቸው ያልረኩት ራይሲ በሻሂድ ሞተሃሪ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን በመከታተል በህግ የሁለተኛ ዲግሪ አግኝተዋል።
ራይሲ ከዚህ በተጨማሪም "በጁሪስፕሩደንስ ኤንድ ፕሪንሲፕልስ ኦፍ ዲፓርትመት ኦፍ ፕራይቬት ሳይትስ " የዶክትሬት ዲግሪ አግኝተዋል። ከእዚያ በኋላ በሰሚናሮች እና በዩኒቨርሲቲዎች ስልጠና ሰጥተዋል።
የስራ ታሪክ
ኢብራሂም ራይሲ በ1980፣ በ20 አመታቸው የካራጅ ከተማ ምክትል አቃቤ ህግ ሆነው ስራ ጀመሩ። ከሁለት አመት በኋላ በሀመዳን ከተማ አቃ ህግ ሆነው ካገለገሉ በኋላ በ1985 የኢራን ከተማ ምክትል አቃ ህግ መሆን ቻሉ።
በ1988 በሺዎች የሚቆጠሩ የፖለቲካ እስረኞችን እጣፋንታ የሚወስነው "የሞት ኮሚቴ" እየተባለ የሚጠራውን እና አለምአቀፍ ውግዘት ያስከተለው የህግ ኮሚቴ አባል ሆኑ።
በ1990 የዋና ከተማዋ ቴህራን አቃቤ ህግ በመሆን የኢራን ኢንስፔክሽን እና ኦርጋናይዜሽን ኃላፊ እስከሆኑበት ጊዜ ድረስ በህግ ዘርፉ ለረጅም ጊዜ ሰርተዋል።
ከእዚያ ቀጥሎ የኢራኑ የህግ ወይም ጁዲሻሪ ፕሬዝደንት ሞሀመድ ሀሺሚ ሻህሮዲ ምክትል አድርገው ሾመዋቸው ከ2005-2015 አገልግለዋል።
በ2016 ጠቅላይ መሪው ራይሲ የአስታን ኩድስ ራዛቪ የተባለውን የምግባረ ሰናይ ድርጅት እንዲመሩ በማድረግ፣ የራይሲን የሙያ ጉዞ ቀየሩባቸው።
ድርጅቱ ጠንካራ ፖለቲካዊ እና ሀይማኖታዊ ተጽዕኖ ያለው ሲሆን ለተለያዩ ፕሮጀክቶች የሚውል ብዙ ገንዘብ የሚቀበል ነው።
ራይሲ በፕሬዝደንትን ታጩ
ኢብራሂም ራይሲ በ2ዐ17 በተካሄደው ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ከሀሰን ሮሃኒ ጋር ተፎካከሩ፤ ነገርግን 38 በመቶ ድምጽ በማግኘት ማሸነፍ አልቻሉም።
ከሶስት አመት በኋላ መጋቢት 7፣2019 አያቶላህ አሊ ከሚኒ አስር አመት ያገለገሉትን ሳድግ ላሪጃኒን በማንሳት የኢራን ጁዲሻሪ ኃላፊ አድርገው ሾሟቸው።
በሐምሌ 2021 የተካሄደውን ምርጫ እስከሚያሸኝፉበት ጊዜ ድረስ የጁዲሻሪው (ፍርድ ቤቶች) ኃላፊ ሆነው የአምስት አመታት ሰርተዋል።
ሐምሌ 19፣2021 በ61.95 በመቶ በማግኘት ስምንተኛው የኢራን ፕሬዝደንት መሆናቸው አወጁ።