የሀገሪቱ መንፈሳዊ መሪ አያቶላህ ካሚኒ የቅርብ ሰው የሚባሉት ሞሀመድ ሞክበር በተደጋጋሚ በምዕራባዊን ማዕቀብ ተጥሎባቸዋል
የኢራን ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲ በ63 ዓመታችው በትናንትናው ዕለት ባጋጠመ የሄሊኮፕተር አደጋ ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል።
በዚህ አደጋ የኢራን ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆሴን አሚራብዶላሂያንም በሄሊኮፕተር አደጋው ህይወታቸው ማለፉን የኢራን መገናኛ ብዙሃንም ዘግበዋል።
ከፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲ እና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆሴን አሚራብዶላሂያንም በተጨማሪ በሄሊኮፐተሩ ውስጥ ተሳፍረው የነበሩ 8 ከፍተኛ ባለስልጣናት እና አብራሪዎችም ህይወታቸው አልፏል።
ይህን ተከትሎ በሀገሪቱ ህገ መንግስት መሰረት አሁን ላይ የኢራን ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት ሞሀመድ ሞክበር ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት ሆነው እንደሚቀጥሉ ተገልጿል፡፡
የ68 ዓመቱ ሞሀመድ ሞክበር የኢራን መንፈሳዊ መሪ አያቶላ ካሚኒ የቅርብ ሰው ናቸው የተባለ ሲሆን ሀገሪቱ በ50 ቀናት ውስጥ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እንደምታካሂድ ይጠበቃል፡፡
የኢራን ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲ ሄሊኮፕተር አደጋ ህይወታቸው አለፈ
ሞሀመድ ሞክባር ከፈረንጆቹ 2021 ጀምሮ የኢራን ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው በመስራ ላይ ሲሆኑ በቀጣዮቹ ቀናት ደግሞ ምርጫ እስከሚካሄድ ድረስ የኢራን ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት ተደርገው እንደሚሾሙ ይጠበቃል፡፡
በደቡባዊ ኢራን ዲዝፉል በተሰኘችው አነስተኛ ከተማ የተወለዱት ሞሀመድ ሞክበር ኢራን የኑክሌር ጦር መሳሪያ እንድትታጠቅ ሲደረጉ የነበሩ ጥረቶችን በመምራት ይታወቃሉ፡፡
በዚህ ጥረታቸውም በምዕራባዊያን ሀገራት በተደጋጋሚ ማዕቀብ የተጣለባቸው ሲሆን ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ማዕቀቦቹ ሁሉ ተነስተውላቸዋል፡፡
ኢራን እንደ ሩሲያ ካሉ ሀገራት ጋር ወታደራዊ ስምምነቶች እንዲኖራት የቴህራንን ልዑክ የሚመሩ ሰው ናቸው የተባሉት ሞሀመድ ሞክበር ከ50 ቀናት በኋላ በሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ላይ ሊሳተፉ እንደሚችል ይጠበቃል፡፡