አሊሬዛ አክባሪ በኢራን ውስጥ በጣም ቁልፍ ከሆኑት የብሪታንያ የስለላ አገልግሎት ወኪሎች አንዱ ነበሩ ተብለዋል
ኢራን ለብሪታንያ በመሰለል ክስ የተመሰረተባቸው የኢራንና እንግሊዝ ጥምር ዜግነት ያላቸውን የቀድሞ ምክትል የመከላከያ ሚንስትር የሞት ፍርድ እንደፈረደች ተነግሯል።
አሊሬዛ አክባሪ በኢራን ውስጥ በጣም ቁልፍ ከሆኑት የብሪታንያ የስለላ አገልግሎት ወኪሎች አንዱ ነበሩ ተብለዋል።
የኢራን የደህንነት ሚንስቴር "አክባሪ ሙሉ በሙሉ እያወቁ ለጠላት የስለላ አገልግሎት መረጃ ሰጥተዋል" ብሏል። ብሪታንያ በአሊሬዛ አክባሪ ላይ የተፈረደውን የሞት ፍርድ "ፖለቲካዊ" በማለት በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠይቃለች።
የብሪታንያ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ጀምስ ክሌቨርሊ አክባሪ እንዲፈቱ ጠይቀዋል።
ክሌቨርሊ በትዊተር ገጻቸው "ኢራን የብሪታኒያ ኢራናዊውን አሊሬዛ አክባሪን ግድያ ማቆም አለባት እና ወዲያውኑ መልቀቅ አለባት" ሲሉ መጠየቃቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
"ይህ በፖለቲካ የተደገፈ በአረመኔ አገዛዝ የተፈጸመ እና ለሰው ልጅ ህይወት ምንም ደንታ የሌለው ተግባር ነው" ሲሉም አክለዋል።
እ.ኤ.አ.በ2019 የታሰሩት አክባሪ በ1980ዎቹ ከኢራን-ኢራቅ ጦርነት ጀምሮ ለአሁኑ የኢራን የደህንነት ም/ቤት አለቃ አሊ ሻምካኒ የቅርብ ሰው ነበሩ ተብሏል።
የሞት ፍርድ የፈረደባቸው የኢራን ጠቅላይ ፍ/ቤት ኑር ኒውስ የተባለው የኢራን የዜና ወኪል ከሀገሪቱ ከፍተኛ የደህንነት ኤጀንሲ ጋር ግንኙነት እንዳለው ዘግቧል።
ብሪታንያን ጨምሮ ከምዕራባውያን ኃያላን መንግስታት ጋር በመቃቃር ለወራት በዘለቀው ጸረ-መንግሥት ተቃውሞ የውጭ ኃይሎች ጣልቃ ገብተውብኛል የምትለው ኢራን ጣምራ ዜግነትን አትቀበልም።