ሩስያ እና ኢራንን ከማዕቀብ የታደገው የንግድ መስመር የትኛው ነው?
3 ሺህ ኪሎሜትሮችን የሚረዝመው አህጉር አቋራጭ የንግድ መስመር ከአውሮፓ ምስራቃዊ ጫፍ እስከ ህንድ ውቅያኖስ ተዘርግቶ በየቀኑ በርካታ መርከቦች ይመላለሱበታል
ሞስኮ እና ቴህራን ቢሊየን ዶላሮችን አውጥተው የከፈቱት የንግድ መስመር የሃያላን ሀገራት ፉክክር የአለም የንግድ ስርአትን በምን መልኩ እንደሚለውጥ ማሳያ ተደርጓል
ሩስያ እና ኢራን ከምዕራባውያን ማዕቀብ የሚታደጋቸውን አህጉር አቋራጭ የንግድ መስመር እየዘረጉ መሆኑ ተነገረ።
ከአውሮፓ ምስራቃዊ ጫፍ እስከ ህንድ ውቅያኖስ 3 ሺህ ኪሎሜትሮችን የሚሸፍነው የንግድ መስመር ወደ ስራ እንዲገባ ሀገራቱ ቢሊየን ዶላሮችን አውጥተዋል።
ብሉምበርግ የሳተላይት ምስሎችን በማያያዝ ባወጣው ዘገባ በርካታ የሩስያና ኢራን መርከቦች በየቀኑ በዚህ መስመር እቃዎችን ጭነው እየተመላለሱ ነው።
ይህ መስመር ሀገራቱን በምዕራባዉያን ከተጣሉባቸው የንግድ ማዕቀቦች የሚከላከል ስለመሆኑም ነው ዘገባው ያነሳው።
የሃያላን ሀገራት ፉክክር በማዕቀብ ናዳ የተጎዱትን ሞስኮ እና ቴህራን ይበልጥ አቀራርቦ የራሳቸውን የንግድ መስመር እንዲዘረጉ አድርጓል።
ሩስያ 1 ቢሊየን ዶላር ወጪ የቮልጋ ወንዝን ከአቮዝ ባህር ጋር ለማገናኘት ጥረት እያደረገች።።
ኢራንም ከሩስያ ጋር የሚያገናኛትን የባህር የየብስና የባቡር መሰረተልማት ለማሳደግ በብርቱው እየሰራች ነው ይላል ዘገባ።
የቻባሃር ወደብ ግንባታ መፋጠንም የንግድ ትስስሩን ያቀላጥፈውል ተብ
ሞስኮ በቴህራን በኩል ህንድ ፣ ምስራቅ እና አፍሪካን ለመድረስ ለምታደርገው ጥረት ሀገራቱ እስከ 25 ቢሊየን ወጪ ለማድረግ መስማማታቸው ተነግሯል።
በሩስያ እና ዩክሬን ጦርነት ለሞስኮ ሸጣለች በሚል ከአሜሪካ ወቀሳው የበረታባት ኢራን ከሩስያ ጋር የምጣኔ ሃብት አላት።።
ቴህራን የሞስኮን የግብርና ምርት ከሚገዙ ሀገራት በሶስተኛ ደረጃ ላ ትቈᛈᛈ የኢራን የኒዩክሌር ማብለያ መሳሪያዎች የመድሃኒት እና የተሽከርካሪዎች ግብአቶችም ከሞስኮ ታስገባለች።።
ይህን ትስስር ለማሳደግ ታዲያ ኢራን ወንዝ ዳርቻ ከ ከ 10 ሚሊየን ዶላር በላይ ያደረገችበትን ወደብ ነው።።
5 ቢሊየን ዶላር የደረሰው የሀገራቱ የንግድ ትስስር የንግድ ቀጠና ሲመሰረት 40 ቢሊየን ዶላር ነው የሚጠበቀው።
በመቶዎች የሚቆጠሩ የሀገራቱ መርከቦችም በአዲሱ መስመር ጉዞ ሲያደርጉ የሚያሳዩ የሳተላይት ምስሎችን ብሉምበርግ አድርጓል።።
ኢራን ከሩስያ ጋር የዘረጋችውን ማዕቀብን የሚያመልጥ የንግድ መስመ ምዕራባውያኑ አይናቸውን ጥለውበታል ተብሏል።
አሜሪካም በ2015 ወደተፈረመው የኢራን የኒዩክሌር ስምምነት የመመለሷ ነገር ያከተመለት ይመስላል።
ኢራን በኒዩክሌር ፕሮግራሟ ፤ ሩስያ ደግሞ በዩክሬኑ ጦርነት ምክንያት ከምዕራቡ አለም የገጠማቸውን ፈተና በጋራ እያለፉበት ያለው መንገድ የአለም ስርአት በአንድ ልዕለ ሃያል ሀገር የመመራቱን ጉዳይ ጥያቄ ውስጥ ከቶታል።
የሩስያ፣ ቻይና እና ኢራን “የምስራቁ ክንፍ”፥ ለምዕራቡ አለም ምላሽ እየሰጠ ይገኛል።