ፖለቲካ
የኢራኑን ፕሬዝዳንት አሳፍራ በከተሰከሰችው ሄሊኮፕተር ዙሪያ ምን አዳዲስ መረጃዎች አሉ?
የኢራኑን ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲን ያሳፈረች ሄሊኮፕተር ላይ አደጋ ደርሷል
የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች አደጋው ያጋጠመበት ስፍራ መድረሳቸውና በህይወት ያለ ሰው ምልክት አለማግኘታቸውን ገልጸዋል
የኢራኑን ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲን ጨምሮ ከፍተኛ የሀገሪቱ ባለስልጣናትን ያሳፈረች ሄሊኮፕተር ላይ ትናንት አመሻሹን አደጋ መድረሱ ይታወቃል።
አደጋው ከአዘርባጃን ጋር በምትዋሰነውና ከቴህራን በ600 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ጆልፋ በተሰኘች ከተማ መድረሱ ተገልጿል።
ፕሬዝዳንት ራይሲን ባሳፈረችው ሄሊኮፕተር ውስጥ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሆሴን አሚራብዶላሂያን እና ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት አብረው ጉዞ ላይ ነበሩ ተብሏል።
- የኢራኑን ፕሬዝዳንት ያሳፈረች ሄሊኮፕተር ላይ "አደጋ" መድረሱ ተነገረ
- ፕሬዝዳንት ራይሲን ባሳፈረችው ሄሊኮፕተር ውስጥ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሆሴን አሚራብዶላሂያን እና ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት አብረው ጉዞ ላይ ተብሏል።
የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ወደ ስፍራው ያቀኑ ሲሆን፤ አደጋው ያጋጠመበት ስፍራ መድረሳቸውና በህይወት ያለ ሰው ምልክት አለማግኘታቸውን ገልጸዋል።
ፕሬዚዳንቱን አሳፍራ ስትጓጓ የነበረችው አሜሪካ ሰራሽ ሄሊኮፕተር ሙሉ በሙሉ በእሳት መውደሟንም ነው የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ሪፖርት የሚያመላክተው።
አሁን እየወጡ ያሉ መረጃዎች ደግሞ የኢራኑን ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሆሴን አሚራብዶላሂያን ጨምሮ በሄሊኮፕረቱ ውስጥ የነበሩ ሁሉም ተሳፋሪዎች ህይወታቸው ማለፉን የሚያመላክቱ ናቸው።