እስራኤልን ይመታሉ ተብለው የሚገመቱ የኢራን ሚሳኤሎች ምን ምን ናቸው?
ባሳለፍነው ሳምንት የኢራን ሁለት ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች ከእስራኤል በተሰነዘረ ጥቃት በሶሪያ መገደላቸው ይታወሳል
ኢራን ከእስራኤል ለደረሰባት ጥቃት የአጸፋ እርምጃ እንደምትወስድ መዛቷ ይታወሳል
እስራኤልን ይመታሉ ተብለው የሚገመቱ የኢራን ሚሳኤሎች ምን ምን ናቸው?
ከስምንት ቀን በፊት የእስራኤል ጦር በሶሪያ መዲና ደማስቆ በሚገኝ ቆንስላ ጽህፈት ቤት ላይ ባደረሰው ጥቃት ሁለት የኢራን አብዮታዊ ዘብ አዛዦችን ጨምሮ ዘጠኝ ሰዎች መገደላቸው ይታወሳል፡፡
የእስራኤልን ጥቃት ተከትሎ ኢራን የአጸፋ እርምጃ እንደምትወስድ የዛተች ሲሆን የኢራን ዜና አገልግሎት እስራኤልን መምታት የሚችሉ ሚሳኤሎችን ይፋ አድርጓል፡፡
ሰጂል የተሰኘው ኢራን ሰራሽ ሚሳኤል ከ2 ሺህ እስከ 2500 ኪሎ ሜትር መጓዝ እንደሚችል የተገጸ ሲሆን በእስራኤል ባሉ ቦታዎች ላይ ጥቃቶችን ማድረስ ያስችላል ተብሏል፡፡
ሌላኛው ኢራን ሰራሽ ሚሳኤል ኮራምሻር የሚሰኝ ሲሆን ይህ ሚሳኤል 2 ሺህ ኪሎ ሜትር ርቀት ውስጥ ያሉ ኢላማዎችን መምታት እንደሚችል ተገልጿል፡፡
በኢራን እና እስራኤል መካከል ያለው ርቀት 1ሺህ 789 ኪሎ ሜትር ሲሆን ኢራን ካሏት ዘጠኝ አይነት ሚሳኤሎች መካከል አምስቱ እስራኤል መድረስ ይችላሉም ተብሏል፡፡
ሶስተኛው ኢራን የታጠቀችው ባሊስቲክ ሚሳኤሎች መካከል ኢማድ የሚባል ሲሆን 2 ሺህ ኪሎሜትር ርቀት ላይ ያለን ኢላማ እንደሚመታ በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡
ሻሃብ የተሰኘው ባሊስቲክ ሚሳኤልም በተመሳሳይ በ2 ሺህ ኪሎ ሜትር ላይ ያለን ኢላማ መምታት እንደሚችል ሲገለጽ ቃድር የተሰኘው ሌላኛው ባሊስቲክ ሚሳኤል ደግሞ 1 ሺህ 950 ኪሎ ሜትር የመጓዝ አቅም አለውም ተብሏል፡፡
ፓቬህ፣ ካይባርሼካን፣ ፋታህ 2 እና ሀጅ ቃሲም የተሰኙት ባሊስቲክ ሚሳኤሎች ከ1 ሺህ 650 እስከ 1450 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ያሉ ኢላማዎችን መምታት እንደሚችሉ በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡
የኢራን ፕሬዝዳንት ጸህፈት ቤት የፖለቲካ ጉዳዮች ሃላፊ የሆኑት ሞሀመድ ጃምሺዲ በኤክስ ገጻቸው አንዳሉት “አሜሪካ በእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ወጥመድ ውስጥ እንዳትገባ ራሷን ከእስራኤል እንድታርቅ እናስጠነቅቃለን“ ሲል ጽፏል፡፡
ኢራን በአሜሪካ ላይ ጥቃት እንዳትሰነዝር መጠየቋን ገለጸች
ለአሜሪካ መልዕክት መላኳን እና መልዕክቱ እንደረሰው የገለጸው ጽህፈት ቤቱ በምላሹም ኢራን በእስራኤል የደረሰባትን ጥቃት እንደ መነሻ በመውሰድ ጥቃት እንዳትሰነዝር ይህ ከሆነ ግን አካባቢው ወደ ከፋ ግጭት ሊያመራ እንደሚችል ምላሽ መስጠቱን አስታውቋል፡፡
የአሜሪካ መከላከያ ተቋም የሆነው ፔንታጎን በበኩሉ እስራኤል በኢራን ኮንጽላ ጽህፈት ቤት ላይ በደረሰው ጥቃት እጁ እንደሌለበት እና ሀላፊነቱን እንደማይወስድ አስታውቋል፡፡
እስራኤል ከኢራን ሊደርስ የሚችል ጥቃት ሊኖር ይችላል በሚል ጦሯን ዝግጁ እንዲሆን ያዘዘች ሲሆን ለወታደሮቿ የሚሰጥ የትኛውንም እረፍት ከልክላለች፡፡