እስራኤል በሶሪያ የኢራን ኢምባሲ ላይ ለሰነዘረችው ጥቃት የአጸፋ እርምጃ እንደምትወስድ እየዛተች ነው
ኢራን በአሜሪካ ላይ ጥቃት እንዳትሰነዝር መጠየቋን ገለጸች፡፡
ከሐማስ ጋር ጦርነት ላይ ነኝ የምትለው እስራኤል ባሳለፍነው ሳምንት በደማስቆ በሚገኘው የኢራን ኢምባሲ ላይ ጥቃት መሰንዘሯ ይታወሳል፡፡
በዚህ ጥቃት የኢራን አብዮታዊ ዘብ ጠባቂ ሁለት ከፍተኛ አዛዦች የተገደሉ ሲሆን ኢራን ለደረሰባት ጥቃት የአጸፋ እርምጃ እንደምትወስድ ዝታለች፡፡
የኢራን ፕሬዝዳንት ጸህፈት ቤት የፖለቲካ ጉዳዮች ሃላፊ የሆኑት ሞሀመድ ጃምሺዲ በኤክስ ገጻቸው አንዳሉት “አሜሪካ በእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ወጥመድ ውስጥ እንዳትገባ ራሷን ከእስራኤል እንድታርቅ እናስጠነቅቃለን“ ሲል ጽፏል፡፡
ይሄው ግለሰብ ዘግይቶ በጻፈው ተጨማሪ መልዕክት ኢራን በአሜሪካ ላይ ጥቃት እንዳትሰነዝር ጠይቃለች የሚል ይዘት ያለው መልዕክት ማሰራጨቱን ተከትሎ በርካታ ሚዲያዎች ይህን እንደ እውነት እንደወሰዱት ተገልጿል፡፡
የአሜሪካ ነጩ ቤተ መንግስት ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት በኢራን በኩል የወጣውን መረጃ ሀሰት ነው ሲል አጣጥሏል፡፡
ኢራን ለሩሲያ በመቶዎች የሚቆጠሩ ባለስቲክ ሚሳኤሎችን መላኳ ተሰማ
ይሁንና ኢራን ለአሜሪካ መልዕክት መላኳን እና መልዕክቱ እንደረሰው የገለጸው ጽህፈት ቤቱ በምላሹም ኢራን በእስራኤል የደረሰባትን ጥቃት እንደ መነሻ በመውሰድ ጥቃት እንዳትሰነዝር ይህ ከሆነ ግን አካባቢው ወደ ከፋ ግጭት ሊያመራ እንደሚችል ምላሽ መስጠቱን አስታውቋል፡፡
የአሜሪካ መከላከያ ተቋም የሆነው ፔንታጎን በበኩሉ እስራኤል በኢራን ኮንጽላ ጽህፈት ቤት ላይ በደረሰው ጥቃት እጁ እንደሌለበት እና ሀላፊነቱን እንደማይወስድ አስታውቋል፡፡
እስራኤል ከኢራን ሊደርስ የሚችል ጥቃት ሊኖር ይችላል በሚል ጦሯን ዝግጁ እንዲሆን ያዘዘች ሲሆን ለወታደሮቿ የሚሰጥ የትኛውንም እረፍት ከልክላለች፡፡