የሚኒስትሩ ስልክ መሰረቅ የውጭ ሰላዮች መረጃ እንዲያገኙ ያስችላቸውል የሚል ስጋት ፈጥሯል
የኢራኑ የወጣቶችና እና ስፖርት ሚኒስቴር ሃሚድ ሳጃዲ በቴህራን በሚገኝ መስጊድ ፊት ለፊት ሚስጥር ያለበት ስልካቸውን መሰረቃቸው ተገለጸ፡፡
የኢራን ሚዲያዎች ሚኒስትሩ ባልታወቁ ሌቦች ስልካቸውን መሰረቃቸውን ዘግበዋል፡፡”አስር ኢራን” የተባለው የኢራን ዌብሳይት እንደዘበው ማንነታቸው ያልታወቁ ሌቦች የኢራኑን የስፖርት እና ወጣቶች ሚኒስትር ስልክ ሰርቀዋል፡፡
ሚኒስትሩ ስልካቸውን የተሰረቁት በሀገሪቱ ታዋቂ በሆነው ጋዜጠኛ ናደር ታሊብዜዳህ ስርአት ቀብር ላይ በተሳተፉበት ወቅት ነው፡፡
ሚኒስትሩ ስልካቸውን የተሰረቁት በኢራን ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን አካባቢ በሚገኘው መስጊድ ፊት ለፊት መሆኑን ዌብሳይቱ ዘግቧል፡፡ዌብሳይቱ ያናገረው ምንጭ፤ ብዙ ሚኒስትሮች በተሳተፉበት መፈጸሙ፤ ክስተቱ ትልቅ የሴኩሪቲ ክተት እንዳለ ያሳያል ብሏል፡፡
የሚኒስትሩ ጥበቃ ቡድን ያሳየው ግዴላሽነት ሚኒስትሩ እንዲሰረቁ ማድረጉን የገለጸው ሚዲያው የሚኒስትሩ መሰረቅ ለውጭ ሰላዮች ጥሩ መረጃ እንዲያገኙ ያስችላቸዋል ተብሏል፡፡