አዲሱ የኢራን ፕሬዝደንት የአሜሪካን ጫና እንደማይቀበሉ ገለጹ
አዲሱ የኢራን ፕሬዝደነት መሱድ ፔዝሽኪያን ኢራን ለአሜሪካ ጫና ሸብረክ እንደማትል ተናግረዋል
ፔዝሽኪያን "ቻይና እና ሩሲያ ፈታኝ በሆነ ጊዜ ከጎናችን ቆመዋል" ብለዋል።
አዲሱ የኢራን ፕሬዝደነት መሱድ ፔዝሽኪያን ኢራን ለአሜሪካ ጫና ሸብረክ እንደማትል ተናግረዋል።
ሀገራቸው ከቻይና እና ሩሲያ ጋር ያላትን ግንኑነት ያነሱት ፕሬዝደንት መሱዱ ፔዝሺኪያን ኢራን ከአሜሪካ የሚመጣ ጫናን አትቀበልም ብለዋል።
በሄሊኮተር አደጋ የመሞቱን ራይሲን ለመተካት በተካሄደው ምርጫ፣ ወግ አጥባቂውን ያሸነፉት እና በአንጻራዊነት ለዘብተኛ የተባሉት ፔዝሺኪያን ኢራን የኑክሌር ጦር መሳሪያ እንደማትፈልግ እና ከጎረቤቶቿ እና አውሮፓ ጋር መነጋገር እንደምትፈልግ ተናግረዋል።
"አሜሪካ...እውነታውን መቀበል አለባት፤ የኢራን መከላከያ አስተምህሮ የኑክሌር ጦር መሳሪያ እንደማያካትት ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጋዜ መረዳት አለባት" ብለዋል "ለመላው አለም የተላለፈ መእልክት" በሚል ርዕስ ባወጡት መግለጫ።
የ69 አመቱ የልብ ጠጋኝ የሆኑት ፔዝሽኪያን ነባራዊ ሁኔታዎችን ከግምት ያስገባ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ እንደሚከተሉ እና በ2015 የኑክሌር ስምምነት ምክንያት ከኃያላን ሀገራት ጋር የተፈጠረውን ውጥረት ለማርገብ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
ነገርግን በሀገሪቱ ከፍተኛ ስልጣን ያላቸው አያቶላህ አሊ ካሚኒ በመሆናቸው፣ ኢራናውያን ፔዝሽኪያን በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት የገቡትን ቃል ስለመፈጸማቸው ይጠራጠራሉ።
ፔዝሽኪያን "ቻይና እና ሩሲያ ፈታኝ በሆነ ጊዜ ከጎናችን ቆመዋል። ለወዳጅነታቸው ከፍ ያለ ዋጋ እንሰጣለን" ብለዋል።
"ሩሲያ ከፍተኛ ዋጋ የምንሰጣት ጎረቤት እና ስትራቴጂካዊ አጋራችን ነች፤ አዲሱ አስተዳደርም ይህንኑ አጠናክሮ ይቀጥላል" ያሉት ፔዝሽኪያን ቴህራን በዩክሬን ያለው ጦርነት እንዲበቃ የሚደረገውን ጥረት ትደግፋለች ብለዋል።
ፔዝሽኪያ "የኢራን ህዝብ መብታችንን እና ጥቅማችንን አስከብረን" በአለም አቀፍ መድረኮች ላይ ገንቢ ሚና እንዲጫወቱ እንደሚፈልግ ገልጸዋል።