የሩዋንዳው ካጋሜ ለ4ኛ ዙር የስልጣን ዘመን ያሸንፉ ይሆን?
በፈረንጆቹ በ1994 በሩዋንዳ የተፈጸመውን የዘርማጥፋት ያስቆመው አማጺ መሪ የነበሩት የ66 አመቱ ካጋሜ ከ2000 ጀምሮ ሀገሪቱን በፕሬዝደንትነት እያገለገሉ ናቸው
የሩዋንዳው ፕሬዝደንት ፖል ካጋሚ በመጭው ሰኞ በሚካሄደው ምርጫ ለአራተኛ ዙር የስልጣን ዘመን ያሸንፋሉ የሚል ግመት ተሰጥቷቸዋል
የሩዋንዳው ፕሬዝደንት ፓል ካጋሜ ለአራተኛ ዙር ያሸንፉሉ የሚል ግምት አግኝተዋል።
የሩዋንዳው ፕሬዝደንት ፖል ካጋሚ በመጭው ሰኞ በሚካሄደው ምርጫ ሁለት ተቀናቃኞቻቸውን በማሸነፍ ለአራተኛ ዙር የስልጣን ዘመን ያሸንፋሉ የሚል ግመት ተሰጥቷቸዋል።
በፈረንጆቹ በ1994 በሩዋንዳ የተፈጸመውን የዘርማጥፋት ያስቆመው አማጺ መሪ የነበሩት የ66 አመቱ ካጋሜ ከ2000 ጀምሮ ሀገሪቱን በፕሬዝደንትነት እያገለገሉ ናቸው።
የምርጫ ኮሚሽኑ ስደስት አቅም ያላቸው ተፎካካሪዎች እንዲወዳደሩ ስላልፈቀደላቸው፣ ካጋሜ አሁን የሚወዳደሩት ከሁለት ተቀናቃኞቻቸው ጋር ብቻ ነው። በሀገሪቱ ህገመንግስታዊ ማሻሻያ ተደርጎ የፕሬዝደንቱን የስልጣን ዘመን የሚገድበው አንቀጽ መነሳቱን ተከትሎ በፈረንጆቹ በ2017 በተካሃደው ምርጫ፣ ካጋሜ 99 በመቶ ድምጽ ማሸነፋቸው ይታወሳል።
ካጋሜ በሰብአዊ መብቶች ጥሰት እና ከዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጋር ባለው ውጥረት ምክንያት አለም አቀፍ ጫና ገጥሟቸዋል።
የሩዋንዳው ፕሬዝደነት ፖል ካጋሜ ለ4ኛ ዙር የስልጣን ዘመን ያሸንፋሉ የሚል ግመት ተሰጥቷቸዋል።
ካጋሜ በዘርማጥፋት ከአንድ ሚሊዮን ሰዎች የተገደሉባተን ሀገር በመገንባት ከፍተኛ አድኖቆት ተችሯቸዋል። ነገርግን ምዕራባውያን ተችዎቻቸው እና የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች፣ ካጋሜን ሚዲያ በማፈን፣ ተቃዋሚዎችን በመግደል እና በጎረቤት ኮንጎ ያሉ አማጺዎችን በመደገፉ ይከሷቸዋል።
ሩዋንዳ በፈረንጆቹ 2022 በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞችን ለመቀበል ያደረገችው ስምምነት አለምአቀፍ ትኩረት እንድትስብ አድርጓታል። አዲሱ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ኪር ስትራመር ስምምነቱን እንደሚሰርዙት ተናግረዋል።
የሩዋንዳ መንግስት የሚቀርቡበትን ክሶች ሁሉ አስተባብሏል።
ካጋሜ በሩዋንዳ ሰላም እና መረጋጋት ለማስቀጠል ቃል ገብተዋል።
"ከእናንተ ጋር ሀገራችን የማታሳካው የለም፤ ምክንያቱም አሁን ላይ ሞኝ ያልሆኑ መሪዎች አሏችሁ" ሲሉ ካጋሜ በምስራቅ ግዛት በተካሄደ ሰልፍ ላይ ለደጋፊዎቻቸው ተናግረዋል።
በምርጫ ኮሚሽኑ እንዲወዳደሩ ፍቃድ የተሰጣቸው የካጋሜ ተቀናቃኞች ፍራንክ ሀሚነዛ እና በ2017ቱ ምርጫ የተወዳደሩት ፊሊፕ ማይማና ናቸው።