ኢትዮጵያ በ10 ሺህ ሰዎች ላይ ጥላው የነበረውን የጉዞ እገዳ አነሳች
በኢትዮጵያ ባለፉት 12 ወራት ውስጥ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ለሆኑ ሰዎች ፓስፖርት መሰጠቱ ተገልጿል
በኢትዮጵያ ፓስፖርት ቤት ለቤት ማደል ሊጀመር ነው ተባለ
በኢትዮጵያ ፓስፖርት ቤት ለቤት ማደል ሊጀመር ነው ተባለ
የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ዓመታዊ አፈጻጸሙን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል፡፡
የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት እንዳሉት በ2016 አመት 1 ነጥብ 1 ሚሊዮን ፓስፖርት ለአመልካቾ መሰጠቱን ተናግረዋል፡፡
ተቋሙ በታሪኩ ይህን መጠን ያለዉ ፓስፖርት ለአገልግሎት ፈላጊዎች ሲሰጥ የመጀመሪያዉ መሆኑን ዳይሬክተሯ ጠቅሰዋል።
ይህ በዚህ እንዳለም ተቋሙ ከፓስፖርት እና ሌሎች አገልግሎት ክፍያዎች 14 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱንም ተናግረዋል።
በቀጣዩ አመት የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት የኢ - ፓስፖርት (E-Passport) አሰራር እንደሚጀምር ይህም የሀሰተኛ ፓስፖርቶችን እና ሰነዶን እንደሚያስቀር ዳይሬክተሯ ገልጸዋል፡፡
ተቋሙ ከነሃሴ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ የፓስፖርት ክፍያ ታሪፍ ላይ ማሻሻያ እንደሚያደርግም አስታውቋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ከቀጣዩ መስከረም ወር ጀምሮ ቤት ለቤት የፓስፖርት እደላ እንደሚጀምርም ገልጿል፡፡
ይህ የቤት ለቤት አገልግሎት ለሁሉም ዜጎች ሳሆን ባለሃብቶች እና ታዋቂ ሰዎች በሚያቀርቡት ጥያቄ መሰረት ነው የተባለ ሲሆን ለዚህም የተለየ ክፍያ ይተመንለታል ተብሏል፡፡
እንዲሁም ባለፉት 30 አመታት ውስጥ ወደ ሀገር ውስጥ መግባትም ሆነ መዉጣት እንዳይችሉ እገዳ ተላልፎባቸው በነበሩ 10 ሺህ ሰዎች ለይ እግድ ማነሳቱ ተገልጿል፡፡