በኢራን የሄሊኮፐተር አደጋ የሞቱ የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት እነማን ናቸው?
ከፕሬዝዳንት ራይሲ በተጨማሪ 4 ከፍተኛ የኢራን ባለስልጣናት ሄሊኮፕተር አደጋ ህይወታቸው አልፏል
በአደጋው ፕሬዝዳንቱን ጨምሮ በሄሊኮፕተሩ ውስጥ ተሳፍረው የነበሩ የ8 ሰዎች ህይወት አልፏል
የኢራኑን ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲን ጨምሮ ከፍተኛ የሀገሪቱ ባለስልጣናትን ያሳፈረች ሄሊኮፕተር ላይ ትናንት አመሻሹን አደጋ መድረሱ ይታወቃል።
አደጋውን ተከትሎም ፕሬዝዳንቱን አሳፍራ ስትጓጓ የነበረችው አሜሪካ ሰራሽ ሄሊኮፕተር ሙሉ በሙሉ በእሳት መውደሟንም ነው የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ሪፖርት የሚያመላክተው።
ይህንን ተከትሎም የኢራን ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲ አበደጋው ህይወታቸው ማለፉን የኢራን ምክትል ፕሬዝዳንት ሞህሴን መንሱሪ አረጋግጠዋል።
በሄሊኮፕተር አደጋው ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲ በተጨማሪም ሌሎች ከፍተኛ የኢራን ባለስልጣንት ህይወታቸው ማለፉ ነው የተገለጸው።
በአደጋው ህይወታቸው ያለፈው ባለስልጣናትም
- የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆሴን አሚራብዶላሂያን
- የምስራቅ አዘርባጃን አስተዳዳሪ ማክ ራህማቲ
- በምስራቅ አዘርባጃን የኢራን ጠቅላይ መሪ ተወካይ ሞሃመድ አሊ አል-ሃሼም
- የፕሬዝዳንቱ ጥበቃ ኃላፊ ማሄዲ ሙሳቪ ናቸው
በተጨማሪም የሄሊኮፕተሩ አብራሪ፣ ረዳት አብራ እና የበረራ አስተናጋጅ በአደጋው ህይወታቸው ማለፉ ተነግሯል።
የሄሊኮፕተር አደጋው ከአዘርባጃን ጋር በምትዋሰነውና ከቴህራን በ600 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ጆልፋ በተሰኘች ከተማ መድረሱ ተገልጿል።
ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲ ከአዘርባጃን በምትዋሰነው የኢራን የድንበር ከተማ ግድብ መርቀው ሲመለሱ የተሳፈሩበት ሄሊኮፕተር ከተራራ ጋር በመጋጨቱ አደጋው እንደደረሰም ተነግሯል።
አሜሪካ ሰራሽ ሄሊኮፕተር ሙሉ በሙሉ በእሳት መውደሟንም ነው የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ሪፖርት የሚያመላክተው።