የኢራን ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲ ሄሊኮፕተር አደጋ ህይወታቸው አለፈ
በአደጋው ፕሬዝዳንቱን ጨምሮ በሄሊኮፐተሩ ውስጥ ተሳፍረው የነበሩ የ8ት ሰዎች ህይወት አልፏል
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆሴን አሚራብዶላሂያንም በሄሊኮፕተር አደጋው ህይወታቸው አልፏል
የኢራን ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲ በ63 ዓመታችው ሄሊኮፕተር አደጋ ህይወታቸው አለፈ።
የኢራኑን ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲን ጨምሮ ከፍተኛ የሀገሪቱ ባለስልጣናትን ያሳፈረች ሄሊኮፕተር ላይ ትናንት አመሻሹን አደጋ መድረሱ ይታወቃል።
አደጋውን ተከትሎም ፕሬዝዳንቱን አሳፍራ ስትጓጓ የነበረችው አሜሪካ ሰራሽ ሄሊኮፕተር ሙሉ በሙሉ በእሳት መውደሟንም ነው የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ሪፖርት የሚያመላክተው።
ይህንን ተከትሎም የኢራን ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲ አበደጋው ህይወታቸው ማለፉን የኢራን ምክትል ፕሬዝዳንት ሞህሴን መንሱሪ አረጋግጠዋል።
የኢራን ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆሴን አሚራብዶላሂያንም በሄሊኮፕተር አደጋው ህይወታቸው ማለፉን የኢራን መገናኛ ብዙሃንም ዘግበዋል።
ከፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲ እና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆሴን አሚራብዶላሂያንም በተጨማሪ በሄሊኮፐተሩ ውስጥ ተሳፍረው የነበሩ 8 ከፍተኛ ባለስልጣናት እና አብራሪዎችም ህይወታቸው አልፏል።
የፕሬዝዳንቱን እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን ህልፈት ተከትሎም የኢራን መንግስት አስቸኳይ ስብሰባ መጥራቱም ነው የተነገረው።
የሄሊኮፕተር አደጋው ከአዘርባጃን ጋር በምትዋሰነውና ከቴህራን በ600 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ጆልፋ በተሰኘች ከተማ መድረሱ ተገልጿል።
ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲ ከአዘርባጃን በምትዋሰነው የኢራን የድንበር ከተማ ግድብ መርቀው ሲመለሱ የተሳፈሩበት ሄሊኮፕተር ከተራራ ጋር በመጋጨቱ አደጋው እንደደረሰም ተነግሯል።
በ63 ዓመታችው ህይወታቸው ያለፈው ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲ በፈረንጆቹ 2021 ነበር የኢራን ፕሬዝዳንት በመሆን ስልጣን የያዙት።