ኢራን በአደጋ ለሞቱት ፕሬዝዳንት ሬይሲ ምትክ ስድስት ዕጩዎችን አዘጋጀች
የቴህራን ከንቲባ አሊረዛ ዛካኒን ጨምሮ የኢራን ኑክሌር ጦር ልማት ተደራዳሪ የነበሩት ሰኢድ ጃሊሊ ከዕጩዎች መካከል ዋነኞቹ ናቸው
የቀድሞው የኢራን ፕሬዝዳንት አህመዲን ነጃድ ለዳግም ፕሬዝዳንትነት የተመዘገቡ ቢሆንም ከዕጩነት ተሰርዘዋል
ኢራን በአደጋ ለሞቱት ፕሬዝዳንት ሬይሲ ምትክ ስድስት ዕጩዎችን አዘጋጀች፡፡
ከአንድ ወር በፊት ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ሬይሲ በኢራን እና አዛርባጂያን ድንበር ላይ የተገነባ የመስኖ ግድብን መርቀው ወደ ቴህራን በመመለስ ላይ እያሉ ባጋጠመ የሂልኮፕተር አደጋ ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል፡፡
ይህን ተከትሎ ሀገሪቱ ለሰኔ 20 ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለማደረግ ፕሮግራም የያዘችው ኢራን እጩ ፕሬዝዳንቶችን ስትመዘግብ ቆይታለች፡፡
የሀገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን ባወጣው የፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ላይ ለመወዳደር 80 እጩ ፕሬዝዳንቶች የተመዘገቡ ቢሆንም የመጨረሻ ስድስት እጩዎችን ይፋ አድርጓል፡፡
ከ20 ቀናት በኋላ በሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ላይ ስድስት ዕጩዎች ለህዝብ ይፋ ተደርገዋል፡፡
በኢራን የተከሰከሰው አሜሪካ ሰራሹ ሄሊኮፕተር “ቤል 212” እውነታዎች
የወቅቱ የሀገሪቱ መዲና ቴህራን ከንቲባ የሆኑት አሊረዛ ዛካኒ፣ የቀድሞው የኢራን ኑክሌር ተደራዳሪ ሳኢድ ጃሊሊ፣ የወቅቱ ምክትል ፕሬዝዳንት አሚር ሁሴን ሀሽሚ፣ የቀድሞው የሀገር ውስጥ ሚኒስትር ሞስጣፋ ፑርሞሃማዲ እና የወቅቱ የምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሞሃመድ ጋሊባፍ እጩ ፕሬዝዳንቶች መካከል ተጠቅሰዋል፡፡
የቀድሞው የኢራን ፕሬዝዳንት ሞሀመድ አህመዲን ነጃድ ድጋሚ ለፕሬዝዳንትነት ለመወዳደር ቢመዘገቡም ሳይሳካለቸው እንደቀረ አል አረቢያ ዘግቧል፡፡
የ67 ዓመቱ የቀድሞው ፕሬዝዳንት አህመደዲን ነጃድ ኢራንን ከ2005 እስከ 2013 ድረስ መምራታቸው ይታወሳል፡፡