የእስራኤልና ሃማስ ጦርነት አዳሩን ምን አዳዲስ ነገሮች ተከስተዋል? አሁንም ምን እየተካሄደ ነው?
እስራኤል 1.1 ሚሊየን የሚሆኑ ፍልስጤማውያን ከሰሜናዊ ጋዛ በ24 ሰዓት ለቀው እንዲወጡ አስጠንቅቃለች
ሃማስ እስራኤል በጋዛ ላይ በእግረኛ ጦር የምታደርገውን ወረራ ለመመከት ዝግጁ ነኝ ብሏል
ሃማስ ባሳለፍነው ቅዳሜ በእስራኤል ላይ ያለተጠበቀ እና ድንገተኛ ጥቃት መሰንዘረሩን ተከትሎ በእስራኤልና በፍልስጤም መካከል የተጀመረው ጦርነት ዛሬ ሰባተኛ ቀኑን ይዟል።
በሃማስ ጥቃት እና በእስራኤል የአየር ድብደባ ከሁለቱም ወገኖች የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ2 ሺህ 800 ማለፉ ተነግሯል።
እስራኤል ባወጣችው መረጃ መሰረት በሃማስ ጥቃት የሞቱ እስራኤላውያን ቁጥር 1300 የደረሰ ሲሆን፤ ከ3 ሸህ 300 በላይ ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል።
የፍልስጤም ባለስልጣናት በሰጡት መረጃ ደግሞ በእስራኤል የአየር ድብደባ የሞቱ ፍልስጤማውያን ቁጥር 1 ሺህ 500 የደረሰ ሲሆን፤ 5 ሺህ 600 ሰዎች ቆስለዋል።
የተመድ የስደቶች ኤጀንሲ እንዳስታወቀው በእስራኤል የአየር ድብደባ 4238 ሺህ ሰዎች ከጋዛ መፈናቀላቸውን አስታውቋል።
በጦርነቱ ያሉ ዋና ዋና ጉዳዮች ምንድናቸው?
እስራኤል በጋዛ በተለይም በሰሜናዊ ክፍል በመጪው ቀናት ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ወታደራዊ ዘመቻ ለማድረግ እየተዘጋጀሁ ነው ብላለች።
በሰሜናዊ ጋዛ የሚኖሩ ፍልስጤማውያን በ24 ሰዓት አውስጥ አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ እስራኤል አዛለች፤ ይህም 1.1 ሚሊየን ዜጎች እዲፈናቀሉ ያደርጋል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እራኤል ሰሜናዊ ጋዛን ለማጽዳት የያዘችው ዘመቻ ከፍተኛ የሆነ ሰብዓዊ ቀውስ ያስከትላል ሲል አስጠንቅቋል።
የሃማስ ወታደራዊ ከንፍ አል-ቃሳም ብርዴግ እስራዔል በምድር ጦር የምታደረገውን ወረራ ለመፋለም ሙሉ አቅም አለኝ ብሏል።
ሂውማን ራይትስ ዎች እስራኤል በጋዛ እና ሊባኖስ ወታደራዊ ዘመቻዋን ስታካሂድ ነጭ ፎስፈረስ ጥይቶችን ተጠቀማለች ሲል ከሰዋል።
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሁሴን አሚራብዶላሂን፤ እስራኤል ጋዛን ማጥቃቷን ከቀጠለች ጦርነቱ ለአዳዲስ ግንባሮች በር ሊከፍት ይችላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
የእስራኤል ጦር ጄቶች ከቅዳሜ ወዲህ በጋዛ ላይ 6 ሺህ ቦምቦችን በጋዛ ላይ የጣለ ሲሆን፤ ፈንጂዎች 4 ሺህ ቶን የሚመዝኑ መሆኑንም የእስራኤል ጦር ቃለ አቀባይ አስታውቀዋል።
ሃማስም ከጋዛ ወደ እስራኤለ የተለያዩ ከተማዎች ላይ የሚያደርጋቸውን የሮኬት ድብደባዎች ቀጥሏል፤ ሃማስ እስካሁን በሺዎች የሚቆጠሩ ሮኬቶችን ወደ እስራኤል ተኩሷል።