በ2023 የነበሩ አበይት የኢኮኖሚ ጉዳዮች ምን ምን ናቸው?
ባንኮች ብድር እንዳይሰጡ መከልከሉ፣ የኢትዮጵያ ብድር ጉዳይ እና የኑሮ ውድነት በዓመቱ ከነበሩ አቤት ጉዳዮች መካከል ዋነኞቹ ነበሩ
ባልተለመደ መልኩ የባንኮች ኪሳራ፣ የወጪ ንግድ ቅናሽ ማሳየት እና ኢትዮጵያ ብሪክስን መቀላቀሏ በተጨማሪነት ዋነኛ የኢኮኖሚ ክስተቶች ናቸው
?በ2023 የነበሩ አበይት የኢኮኖሚ ጉዳዮች ምን ምን ናቸው
የፈረንጆቹ 2023 ዓመት በርካታ የኢኮኖሚ ክስተቶች የተከሰቱበት ዓመት ሲሆን አልዐይን የሀገር ውስጥ እና የውጭ አበይት የኢኮኖሚያዊ ክስተቶችን እንደሚከተለው አሰናድቶላችኋል፡፡
የሀገር ውስጡን ስናስቀድም የሳፋሪኮሙ ድጅታል መገበያያ ገንዘብ ኤምፔሳ በ150 ሚሊዮን ዶላር የኢትዮጵያን ድጅታል ገበያ መቀላቀሉ በዓመቱ ውስጥ ከነበሩ አቤት ክስተቶች መካከል አንዱ ነበር፡፡
ሌላኛው የሀገር ውስጥ ዋነኛ ክስተት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቢሾፍቱ አቅራቢያ በ5 ቢሊዮን ዶላር ኤርፖርት ሲቲ እገነባለሁ ማለቱ ነበር፡፡
በኢትዮ ቴሌኮም የተዋወቀው የ5ጂ ኔትወርክ አገልግሎት ሌላኛው የዓመቱ ክስተት ሲሆን የኦሬንጅ የተሰኘው የአውሮፓ ግዙፉ የቴሌኮም ኩባንያ ወደ ኢትዮጵያ ገበያ የመግባት እቅዱን መሰረዙም ሌላኛው የሀገር ውስጥ ዋና ክስተት ሆኖ አልፏል፡፡
ኢትዮጵያ ከዚህ በፊት የተበደረቻቸውን ብድሮች ለመክፈል መቸገሯ፣ የመክፈያ ጊዜ ይራዘምልኝ ማለቷ፣ ዓለም ባንክ እና አይኤምኤፍን አዲስ ብድር ስጡኝ ማለቷ፣ አዲስ ከ10 ዓመት በፊት በቦንድ የሰበሰበችውን የ1 ቢሊዮን ዶላር ወለድ አለመክፈሏ እና ዛምቢያን እና ጋናን ተከትላ ብድራቸውን መክፈል ከማይችሉ ሀገራት ተርታ መመደቧም ሌላኛው የአመቱ አበይት ክስተቶች ናቸው፡፡
ባልተለመደ መልኩ የኢትዮጵያ ባንኮች ኪሳራ ማስመዝገባቸው በዓመቱ ከነበሩ አቤት የኢኮኖሚ ክስተቶች መካከል ዋነኛው ጉዳይ ሲሆን ብሔራዊ ባንክ ባንኮች ለደንበኞቻቸው በሚሰጡት ብድር ላይ ገደብ መጣሉም የዓመቱ ክስተቶች ሆነው አልፈዋል፡፡
በ2015 ዓ.ም የነበሩ አበይት ክስተቶች ምን ምን ነበሩ?
በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ምክንያት አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የጣለችው የበጀት ድጋፍ ማዕቀቦች በፕሬዝዳንት ባይደን ትዕዛዝ ማዕቀቡ ለአንድ ዓመት መራዘሙ እየተጠናቀቀ ባለው 2023 ዓመት ውስጥ ከተከሰቱ አበይት የኢኮኖሚ ክስተቶች መካከል ዋነኛው ነበር፡፡
ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ልማት ባንክ ዓመታዊ ክፍያ ጋር በተያያዘ ሰራችው የተባለው ስህተት እና ግጭትም በዓመቱ ውስጥ ጆሮ ገቢ ከነበሩ ጉዳዮች መካከል አንዱ ሲሆን እና የኢትዮጵያ ግጭት
የነዳጅ ፍጆታ ግዢ ክፍያ ሙሉ ለሙሉ በድጅታል ይከፈሉ መባሉ፣ ኢትዮጵያ ብሪክስን መቀላቀሏ እንዲሁም የኢትዮጵያ አየር መንገድ 78 አውሮፕላኖችን ለመግዛት ከቦይንግ እና ኤርባስ ጋር የግዥ ስምምነት መፈራረሟም ተጨማሪ የዓመቱ አበይት ክስተቶች መካከል ተጠቃሽ ናቸው፡፡
እንዲሁም መነሻውን አውሮፓ ያደረገው ያንጎ የተሰኘው የሜትር ታክሲ ኩባንያ የኢትዮጵያን ገበያ መቀላቀሉ፣ የኢትዮጵያ የወጪ ንግድ ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ጉድለት ማሳየቱ፣ ጤፍን ጨምሮ የምግብ ምርቶች ዋጋ መናር፣ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በትግራይ አገልግሎቱን ለመጀመር መወሰኑ፣ የሩሲያ ላዳ መኪናዎች ኢትዮጵያ ውስጥ መመረት ሊመረቱ እንደሆነ መገለጹ እና ኢትዮጵያ የጀርመኑ ቮልስዋግን ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ወደ ሀገሯ እንዳይገባ እገዳ መጣሉ እየተጠናቀቀ ባለው የፈረንጆቹ 2023 ዓመት ውስጥ ከነበሩ ክስተቶች መካከል ዋነኞቹ ናቸው፡፡
በባንኮች የጥሬ ገንዘብ እጥረት ማጋጠሙ፣ ኢትዮጵያ አባይ የተሰኘች የንግድ መርከብ ከቻይና መግዛቷ እና የኤክሳይስ ታክስ ህግን በማሻሻል በገቢ ምርቶች ላይ የታክስ ቅናሽ መደረጉም በዓመቱ ከነበሩ ዋና ዋና የኢኮኖሚ ክስተቶች መካከል አበይቶች ነበሩ፡፡
በዓለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚደርሱ ጉዳቶችን ለመከላከል የተካሄደው ኮፕ 28 ጉባኤ ዋነኛው ነበር፡፡
የነዳጅ እና ስንዴ ዋጋ በየጊዜው መናር፣ በተለያዩ ምክንያቶች ተፈላጊነቱ ተቀዛቅዞ የነበረው የቢትኮይን ዋጋ ማንሰራራቱ፣ የቻይና ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የዓለምን ገበያ እየተቆጣጠሩ መምጣታቸው እና አሜሪካ እና አውሮፓ ኩባንያዎቻቸው በቻይና ምክንያት ከውድድር እንዳይወጡባቸው የወሰዷቸው የመከላከያ እርምጃዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ ከነበሩ ክስተቶች መካከል ዋነኞቹ ናቸው፡፡
በኮሮና ቫይረስ እና በዩክሬን-ሩሲያ ጦርነት ምክንያት የአውሮፓ ሀገራት ኢኮኖሚ መቀዛቀዝ ማሳየት፣ የዓለም ቢሊየነሮች እና ሚሊየነሮች ቁጥር መቀነስ በ2023 ዓመት የነበሩ አበይት ክስተቶች መካከል ዋነኞቹ ናቸው፡፡
እንዲሁም የብሪክስ ሀገራት አዲ የዓለም ኢኮኖሚ ስርዓት ለመገንባት ስራ መጀመራቸውን መግለጻቸው፣ አሜሪካ ዜጎቿ በቻይና ኢንቨስት እንዳያደርጉ የሚከለክል ህግ ማጽደቋ፣ በርካታ የዓለማችን ቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ሰራተኞቻቸውን በገፍ መቀነሳቸው፣ የዶላር ፍላጎት መቀነስ፣ ሀገራት በየራሳቸው መገበያያ ገንዘብ ለመገበያየት መፈለግ፣ የጥቁር ባህር እህል ትራንስፖርት በሩሲያ መቋረጥ፣ እና የቀይ ባህር ትራንስፖርት ከመቼውም ጊዜ በላይ ስጋት ላይ መውደቅ ሊጠናቀቅ ቀናት በቀሩት የፈረንጆቹ 2023 ዓመት ከነበሩ አበይት የኢኮኖሚ ክስተቶች መካከል ዋነኞቹ ሆነዋል፡፡