የአሜሪካና የአውሮፓ ሀገራት መሪዎች በኢራን የኒውክለር ስምምነት ዙሪያ መነጋገራቸውን ገለጹ
ኢራን ስምምነቱን ወደ ተግባር ለማዋል የሚደረገው ጉዞ መዘግየቱን ገልጻለች
የ2015 ቱን ስምምነት ውድቅ ያደረጉት ትራምፕ ነበሩ
የአሜሪካ እና የአውሮፓ ሀገራት መሪዎች በኢራን የኒውክለር ስምምነት ላይ ውይይት ማድረጋቸውን አስታወቁ፡፡
የሀገራቱ መሪዎች የኢራን የኒውክለር ስምምነት በድጋሚ ተግባራዊ እንዲሆን የሚያስችል ንግግር ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡ ውይይት ያደረጉት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን፤ የብሪታኒየው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን፤ የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮንና የጀርመኑ መራሄ መንግስት አላፍ ሾልዝ ናቸው፡፡
የአሜሪካ ቤተ መንግስት (ኋይት ሃውስ) ባወጣው መግለጫ መሪዎቹ ኢራን ቀጠናውን እየረበሸት መሆኑን ገልጾ ከዚህ ድርጊቷ እንድትታቀብ የጋራ ስራ ይጠይቃል ብሏል፡፡
መሪዎቹ ዋነኛ የውይይት አጀንዳቸው ዩክሬን የነበረች ቢሆንም ይመለሳል ስለተባለው የ 2015 የኒውክለር ስምምነት በሰፊው ተወያይተዋል ተብሏል፡፡
ውይይት ያደረጉት የአሜሪካ፣ ብሪታኒያ፣ ፈረንሳይና ጀርመን መሪዎች ስለመካከለኛው ምስራቅ ጉዳይ ቢወያዩም፤የውይይቱ ሁኔታ ግን በዝርዝር አልተጠቀሰም፡፡
አሜሪካና የአውሮፓ ሀገራት በ 2015 ከኢራን ጋር ያደረጉት የኒውክለር ስምምነት በቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ እንዲሰረዝ ተደርጎ ነበር፡፡ የአሁኑ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ሀገራቸውን ወደ 2015 የኒውክለር ስምምነት እንደሚመልሷት መናገራቸው ይታወሳል፡፡
በ 2015 የተፈረመው የኒውክለር ስምምነት በድጋሚ ተግባር ላይ እንዲውል ለማድረግ ሀገራቱ ንግግር ጀምረዋል፡፡ ስምምነቱ ኢራን ኒውክለርን ለሰላማዊ አገልግሎት ማለትም ለህክምና መጠቀም በምላሹ ደግሞ ማዕቀቦች እንዲነሱላት የሚያደርግ ስምምነት ነው፡፡
ምንም እንኳን በአንድ ወገን ያሉት የስምምነቱ ፈራሚዎች እየተነጋገሩ መሆኑን ቢገልጹም፤ ኢራን ግን ስምምነቱን ወደ ተግባር ለመመለስ ጊዜ እየወሰዳችሁ ነው በሚል ቅሬታ አቅርባለች፡፡