ኢራን በሁለት ሳምንት ውስጥ የኑክሌር ቦምብ ግብዓት እንደምታሟላ ተገለጸ
በአሜሪካ የተካሄደው ዓለም አቀፍ የደህንነት ጉባኤ ላይ ኢራን ዋነኛ አጀንዳ ሆናለች
አስፐን የተሰኘው የጸጥታ እና ደህንነት ጉባኤ በአሜሪካ ኮሎራዶ ተካሂዷል
ኢራን በሁለት ሳምንት ውስጥ የኑክሌር ቦምብ ግብዓት እንደምታሟላ ተገለጸ፡፡
ከምዕራባዊን ጋር ሆድና ጀርባ የሆነችው ኢራን በመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ዋነኛ የስጋት ምንጭ መሆኗን አሜሪካ አስታውቃለች፡፡
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አንቶኒ ብሊንከን በኮሎራዶ በተካሄደ የጸጥታ እና ደህንነት ጉባኤ ላይ ተገኝተው እንዳሉት ኢራን በአንድ አልያም በሁለት ሳምንት ውስጥ የኑክሌር ቦምብ መስራት የሚያስችላትን ግብዓት ታሟላለች ብለዋል፡፡
ሚኒስትሩ አስፐን በተሰኘው ዓለም አቀፍ የደህንነት ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር አሁን ያለንበት ቦታ ትክክለኛው አይደለም ያሉ ሲሆን ሀገሪቱ ስለ ኢራን ኑክሌር ጉዳይ መሰል አስተያየት ሲሰጡ ይህ የመጀመሪያቸው ነው ተብሏል፡፡
ኢራን አሜሪካ 7 ቢሊዮን ዶላር ካሳ እንድትከፍላት ጠየቀች
ኢራን እስካሁን የኑክሌር ቦምብ አልታጠቀችም የሚሉት ብሊንከን ጉዳዩ በጥንቃቄ መከታተል ይኖርብናል ሲሉም ተናግረዋል ሲል ሲኤንኤን ዘግቧል፡፡
የአሜሪካ ፖሊሲ ኢራን ኑክሌር ቦምብ እንዳትታጠቅ ነው ያሉት ብሊንከን እስካሁን ኢራን እቅዷን እንዳታሳካ ዲፕሎማሲን ስትከተል መቆየቷንም ተናግረዋል፡፡
ከአንድ ዓመት በፊት የአሜሪካ ከፍተኛ የመከላከያ አመራር ኢራን እስካሁን በ12 ቀናት ውስጥ አንድ የኑክሌር ቦምብ መስራት የሚያስችል ግብዓት መሰብሰቧን ተናግረው ነበር፡፡
የፕሬዝዳንት ባይደን አስተዳድር ከኢራን ጋር በሶስተኛ ወገን በኩል ስትደራደር የቆየ ሲሆን በተለይም በፈረንጆቹ 2018 ላይ በዶናልድ ትራምፕ አስተዳድር ዘመን የተሰረዘው የኢራን ኑክሌር ስምምነትን ዳግም ለማስጀመር ሲወያዩ እንደቆዩም በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡
ይሁንና በ2022 በዓለም አቀፉ አቶሚክ ሀይል ምርመራ ወቅት ኢራን በድብቅ ዩራኒየም እያበለጸገች መሆኗን የሚያሳይ ፍንጭ ማግኘቱን ተከትሎ የሁለትዮሽ ውይይቱ ተቋርጧል ተብሏል፡፡
የእስራኤል- ሐማስ ጦርነት ላይ አሜሪካ በቀጥታ መሳተፏን ተከትሎ በኢራን ይደገፋሉ የሚባሉ ታጣቂዎች በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ የአሜሪካ ወታደራዊ ማዘዣዎችን ኢላማ አድርገዋል፡፡