ኢራን እስራኤል ጥቃት የምትሰነዝርባት ከሆነ የከፋ አጸፋዊ እርምጃ እንደምትወስድ አስጠነቀቀች
ባለፈው ሳምንት ኢራን ወደ እስራኤል ከ180 በላይ የባለስቲክ ሚሳይሎችን አስወንጭፋለች
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢራን በጽዮናዊ አገዛዝ ውስጥ ልትደርስባቸው የምትችላቸውን ኢላማዎች "ጠላቶቻችን" ያውቃሉ ብለዋል
ኢራን እስራኤል ጥቃት የምትሰነዝርባት ከሆነ የከፋ አጸፋዊ እርምጃ እንደምትወስድ አስጠነቀቀች።
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒርትር እስራኤል በየትኛውም የኢራን መሰረተሌማት ላይ ጥቃት የምትፈጽም ከሆነ ከባድ የአጸፋ ምላሽ እንደሚያጋጥማት አስጠንቅቀዋል።
ባለፈው ሳምንት ኢራን ወደ እስራኤል ከ180 በላይ የባለስቲክ ሚሳይሎችን አስወንጭፋለች።
ጥቃቱን ተከትሎ እስራኤል በኢራን ላይ የበቀል እርምጃ እወስዳለሁ ስትል ዝታለች።
"ጽኖናዊ አገዛዝ(እስራኤል) የኢራንን ጉልግበት እንዳይፈታተነው እንመክራለን። በሀገራችን ላይ ጥቃት የሚፈጸም ከሆነ ምላሻችን የከፋ ይሆናል" ሲሉ አርቃች በቴሌቪዥን ባስተላለፉት መልእከት ተናግረዋል።
ማንኛውም በኢራን መሰረተልማት ላይ ለሚፈጸም ጥቃት ጠንካራ ምላሽ እንደሚሰጥ የገለጹት ሚኒስትሩ ኢራን በጽዮናዊ አገዛዝ ውስጥ ልትደርስባቸው የምትችላቸውን ኢላማዎች "ጠላቶቻችን" ያውቃሉ ሲሉ አክለዋል።
የኢራን የነዳጅ ሚኒስትር የሀገሪቱ ዋነኛ የኤክስፖርት ጣቢያዎች መገኛ ወደሆነችው ካርግ ደሴት አቅንተዋል። ሚኒስትሩ በደሴቷ በዛሬው እለት ከባህር ኃይል አዛዦች ጋር መወያየታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን እስራኤል እንዴት ምላሽ መስጠት እንዳለባት አልወሰነችም ብለው እንደማያስቡ ተናግረዋል።
የእስራኤል ጠቅላይ ሚነስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በኢራን ጥቃት ማግስት በሰጡት መግለጫ "ኢራን ከባድ ስህተት ሰርታለች፤ ዋጋ ትከፍላለች" ሲሉ ነበር እንደሚበቀሏት የዛቱት።
ኔታንያሁ በተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ላይም የእስራኤል ረጅም እጅ ኢራን ውስጥ የማይደርስበት ቦታ የለም ሲሉ ማስፈራራታቸው ይታወሳል።