ጦሩ እንደገለጸው የፍልስጤሙ ታጣቂ ሀማስ በደቡባዊ እስራኤል ጥቃት በሰነዘረበት ወቅት አሸባሪዎች በአየር ድንበር ጥሰው እንዲገቡ በመምራት ትልቅ ሚና ተጫውቷል
እስራኤል የሀማስን አየር ኃይል መሪ ገደልኩ አለች።
የእስራኤል ጦር በጋዛ እያካሄደ ባለው የአየር ጥቃት የሀማስን የአየር ኃይል አዛዥ ሙራድ አቡ ሙራድን መግደሉን አስታውቋል።
ጦሩ እንደገለጸው የፍልስጤሙ ታጣቂ ሀማስ በደቡባዊ እስራኤል ጥቃት በሰነዘረበት ወቅት አሸባሪዎች በአየር ድንበር ጥሰው እንዲገቡ በመምራት ትልቅ ሚና ተጫውቷል።
ጦሩ ትናንት በወሰደው እርምጃ በርካታ የሀማስ ይዞታዎችንም መምታቱን ገልጿል።
ሀማስ ተገድሏል ስለተባለው የአየር ኃይል መሪ ጉዳይ ያለው ነገር የለም።
ሀማስ በሺዎች የሚቆጠሩ ሮኬቶች በማዝነብ እና በታጣቂዎቹ በመታገዝ በ50 አመታት ውስጥ ከባድ የተባለ ጥቃት በእስራኤል ላይ አድርሷል።
ሀማስ የእስራኤልን ድንበር በመጣስ ጥቃት ከሰነዘረ አንድ ሳምንት አስቆጥሯል።
በጥቃቱ የተቆጣችው እስራኤል ጦርነት በማወጅ የሀማስ ይዞታ በሆነችው ጋዛ ላይ መጠነሰፊ ጥቃት አድርሳለች፣ በማድረስ ላይም ትገኛለች።
ሀማስን ከምደረ ገጹ አጠፋለሁ ያለችው እስራኤል ከትናንት በስትያ 1.1 ሚሊዮን የሚሆኑ የሰሜን ጋዛ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን እንዲለቁ ባስጠነቀቀችው መሰረት፣ ነዋሪዎች እየተሰደዱ ይገኛሉ።
እስራኤል በተከበበችው ጋዛ የምታደርገው የአየር ድብደባ ሲቀጥል የሰሜን ጋዛ ነዋሪዎች በመኪና፣ በጭነት መኪና እና በአህያ ጓዛቸውን ጭነው ቀያቸውን ለቀው እየተሰደዱ መሆኑን ስካይ ኒውስ ዘግቧል።
በእስራኤል እና ሀማስ ጦርነት እስካሁን በፍልስጤም በኩል 1900 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን በእስራኤል በኩል ደግሞ 1300 ሰዎች ተገድለዋል።
ሀማስ ግጭቱን ለማቆም ቢፈልግም እስራኤል ማጥቃቷን አጠናክራ ቀጥላለች።