የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በወሲብ ቅሌት እየተፈተነ መሆኑ ተገለጸ
በአሜሪካ ታሪክ እስካሁን ስምንት ፕሬዝዳንቶች ከወሲብ ጋር በተያያዘ ክስ ተመስርቶባቸው ያውቃል
ከአንድ ዓመት በኋላ በሚካሄደው ምርጫ ላይ ዋነኛ እጩ እንደሚሆኑ የሚጠበቁት ዶናልድ ትራምፕ ክስ ሊመሰረትባቸው ነው ተብሏል
የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በወሲብ ቅሌት እየተፈተነ መሆኑ ተገለጸ።
አሜሪካንን ከፈረንጆቹ 2016 እስከ 2020 ድረስ በፕሬዝዳንትነት የመሩት ዶናልድ ትራምፕ ክስ ሊመሰረትባቸው እንደሆነ ተገልጿል።
ዶናልድ ትራምፕ በማንሀተን አቃቢ ህግ ክስ ይመሰረትባቸዋል የተባለ ሲሆን በፈረንጆቹ 2006 ላይ ስቶርሚ ዳንኤልስ ከተባለች የወሲብ ፊልም ተዋናይት ጋር ወሲብ መፈጸማቸው ተገልጿል።
- ዶናልድ ትራምፕ ከተከሰስኩ በአሜሪካ ሞትና ውድመት ይከሰታል ሲሉ አስፈራሩ
- ትራምፕ ዛሬ በቁጥጥር ስር ሊውሉ ይችላሉ ተብሏል፤ የአሜሪካ ፖሊስ በተጠንቀቅ ላይ ነው
የቀድሞ ፕሬዝዳንት ጉዳያቸው ወደ ህዝብ ጆሮ እንዳይደርስ በሚልም 130 ሚሊዮን ዶላር ከፍለዋልም ተብሏል።
በጠበቃቸው በኩል ገንዘቡን ከፍለዋል የተባሉት ዶናልድ ትራምፕ ክፍያውን እንደከፈሉ በ2018 ዳንኤልስ ለሚዲያዎች ይፋ አድርጋለች።
ዶናልድ ትራምፕ ድርጊቱን በተደጋጋሚ የካዱ ቢሆንም ስቶርሚ ዳንኤልስ ግን ከቀድሞው ፕሬዝዳንት ጋር ወሲብ መፈጸማቸውን በመናገር ላይ ናቸው።
የማንሀተን አቃቢ ህግም በዶናልድ ትራምፕ ላይ ክስ እንደሚመሰርት ማሳወቁን ተከትሎ ጉዳዩ ትኩረትን ስቧል።
ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው የማንሀተን አቃቢ ህግ ድርጊት በፕቴዝዳንታዊ ምርጫው እንዳልወዳደር በማሰብ ነው ብለዋል።
ዶናልድ ትራምፕ ክስ ከተመሰረተባቸው ከወሲብ ቅሌት ጋር በተያያዘ ክስ የተመሰረተባቸው ስምንተኛው ፕሬዝዳንት እንደሚሆኑ ተጠቅሷል።