ኢራን ከእስራኤል ጋር ግንኙነት ያላትን መርከብ ሰራኞተች እንደምትለቅ ገለጸች
ኤምኤስሲ አይረስ የተባለችው እቃ ጫኝ መርከብ በሆርመዝ ባህረ ሰላጤ የተያዘችው ከሁለት ሳምንታት በፊት ነበር
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከእስራኤል ጋር ግንኙነት አላት በሚል ተይዛ የነበረችው መርከብ ሰራተኞች ይለቀቃሉ ብሏል
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከእስራኤል ጋር ግንኙነት አላት በሚል በኢራን ሪቮሉሽናሪ ጋርድ ተይዛ የነበረችው መርከብ ሰራተኞች እንደሚለቀቁ መግለጹን ሮይተርስ ዘግቧል።
ኤምኤስሲ አይረስ የተባለችው እና የፖርቹጋል ሰንደቅ አላማ ስታውለበልብ የነበረችው 25 ሰራተኞች ያሏት እቃ ጫኝ መርከብ በሆርመዝ ባህረ ሰላጤ የተያዘችው ከሁለት ሳምንታት በፊት ነበር።
- የኢራን ኮማንዶ ጦር ከእስራኤል ጋር ግንኙነት አላት ያላትን መርከብ ያዘ
- የግብጽ ልኡክ ቡድን በተኩስ አቁም እና ታጋቾች ጉዳይ ለመነጋገር እስራኤል መግባቱ ተነገረ
ኢራን መርከቧን የያዘችው በሶሪያ ደማስቆ በሚገኘው ኢምባሲዋ ላይ ጥቃት በማድረስ ሁለት ጀነራሎቿን ጨምሮ ሰባት ወታደሮቿን በመግደል ተጠያቂ ያደረገቻትን እስራኤልን እንደምትበቀል ከዛተች ከጥቂት ቀናት በኋላ ነው።
ኢራን ወሳኝ የሆነውን የመርከብ መተላለፊያ ልትዘጋው እንደምትችልም ተናግራ ነበር።
ከእስራኤል ጋር እየተዋጋ ላለው ሀማስ አጋርነታቸውን የገለጹት የየመን ሀውቲ ታጣቂዎች በቀይ ባህር እና በኤደን ባህረሰላጤ የሚያደርሱት ተደጋጋሚ ጥቃት የንግድ መርከቦችን እንቅስቃሴ አስተጓጉሏል።
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆሴን አሚርአብዶላሂያን ከፓርቹጋል አቻቸው ጋር ባደረጉት የስልክ ውይይት ሰራተኞች ሰብአዊ ክብር በጠበቀ መልኩ እንደሚያዙ እና በቴህራን ለሚገኘው አምባሳደራቸው እንደሚተላለፉ መናገራቸው ተገልጿል።
እንደዘገባው ከሆነ ሰራተኞቹ መቼ እንደሚለቀቁ አልታወቀም።
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር 'አየርስ' በቁጥጥር ስር የዋለችው የማሪታይም ህግን በመጣስ እና ከእስራኤል ጋር ግንኙነት እንዳላት እርግጠኛ በመሆናችን ነው ብለዋል።
ኤምኤስሲ አይረስን የተከራየው ታዋቂው እስራኤላዊ ባለሀብት ኢያል ኦፈር ድርሻ ካለው ዞዲያክ ማሪታይም ኩባንያ ነው።