አለምአቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ሰራተኞቹ የኢራንን የኑክሌር ጣቢያዎች መቆጣጠር ማቆማቸውን ገልጿል
ኢራን በእስራኤል ላይ ጥቃት ማድረሷን ተከትሎ የኑክሌር ጣቢያዎቿን ዘግታለች።
አለምአቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ(አይኤኢኤ) በእስራኤል እና ኢራን መካከል ቀጣናዊ ውጥረት በመፈጠሩ ምክንያት ሰራተኞቹ የኢራንን የኑክሌር ጣቢያዎች መቆጣጠር ማቆማቸውን በትናንትናው እለት ገልጿል።
የኤጀንሲው ኃላፊ ራፋኤል ማሪያኖ ግሮሲ ኒው ዮርክ በተካሄደው የተመድ ስብሰባ በተገኙበት ወቅት ለጋዜጠኞች "...በኢራን የሚገኙት ተቆጣጣሪ ሰራተኞቻችን ሁሉም የኑክሌር ጣቢያዎች የጸጥታ ሁኔታውን ታሳቢ በማድረግ ተዘግተው እንደሚቆዩ በኢራን መንግስት ተነግሯቸዋል" ብለዋል።
ግሮሲ እንደገለጹት ጣቢያዎቹ ሰኞ እለት ለተቆጣጣሪዎች ሊከፈቱ የነበረ ቢሆንም ሁኔታው እስከሚረጋጋ ለመጠበቅ መገደዳቸውን ተናግረዋል።
መዘጋቱ በቁጥጥር ስራቸው ላይ ብዙ ተጽዕኖ እንደማይኖረው የገለጹት ግሮሲ ጥቃት ከማድረስ መቆጠብ ያስፈልጋል ብለዋል።
ኢራን ባለፈው ቅዳም ሌሊት 300 ሚሳይሎችን እና ድሮኖችን አስወንጭፋለች። ጥቃቱ ከአነስተኛ የንብረት ጉዳት በስቀር በሰው ህይወት ላይ ምንም ጉዳት አላደረሰም።
ኢራን በእስራኤል ላይ ይህን ጥቃት ያደረሰችው እስራኤል ሳታደርሰው አትቀርም በተባለ ጥቃት በሶሪያ ደማስቆ የሚገኘው ኢምባሲዋ በመጠቃቱ እና በግቢው የነበሩ ሁለት ጀኔራሎችን ጨምሮ ሰባት ከፍተኛ ወታራዊ ባለሙያዎቿ በመገደላቸው መሆኑን ገልጻለች።
እስራኤል ኢራን ለፈጸመችው ጥቃት ምላሽ እንደምትሰጥ ዝታለች።
የእስራኤል ጦር አዛዥ ሄርዚ ሀለቪ እስራኤል ምላሽ ትሰጣለች ብለዋል።
"ወደ እስራኤል ግዛት በርካታ ሚሳይሎችን እና ድኖሮችን የማስወንጨፍ ተግባር ምላሽ ያስፈልገዋል" ሲሉ የተወሰነ ጉዳት ባጋጠመው እና በደቡብ እስራኤል በሚገኘው በነቫቲም የአየር ኃይል ቤዝ ተገኝተው ተናግረዋል።
እስራኤል የአጸፋ ምላሽ ከመስጠት እንድትቆጠብ አለምአቀፍ ጫና እየተደረገባት ነው።
የአውሮፖ ህብረት የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ጆሴፍ ቦሬል "ገደል አፋፍ ላይ ነው ያለነው" ስሆነም "የኋላ ማርሽ ረግጠን መመለስ አለብን" ብለዋል።
የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን፣ የጀርመን መራሄ መንግስት ኦላፍ ሾልዝ፣ የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሮን ተመሳሳይ መልእክት አስተላልፈዋል። አሜሪካ እና የተመድ ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝም እስራኤል ምላሽ ከመስጠት እንድትቆጠብ ጥሪ አቅርበዋል።
አጋሯን ኢራንን በይፋ ከመተቸት የተቆጠበችው ሩሲያም ሁለቱም ወገኖች ግጭት ከማባባስ እንዲቆጠቡ አሳስባለች።
"ግጭት በማባባስ ማንም ተጠቃሚ አይሆንም" ብለዋል የክሬሚሊን ቃል አቀባይ ዲሜትሪ ፔስኮቭ።
ቻይና፣ ኢራን ጉዳዩን በብልሃት እንደምትይዘው እና ተጨማሪ ቀጣናዊ ቀውስ እንዳይፈጠር እንደምታደርግ ያላትን እምነት ገልጻለች።