ኢራን ጫና እያደረሰባት ከአሜሪካ ጋር የኑክሌር ድርድር አታደርግም- ፕሬዝደንት ፔዝሽኪያን
ኢራን የኑክሌር ጦር መሳሪያ እንዳይኖራት ለረጅም ጊዜ ክልከላ ተጥሎባት ነበር

ኢራን የኑክሌር ስራዋን ያፋጠነችው በ2015 ከስድስት ኃያላን ሀገራት ጋር የገባችውን የኑክሌር ስምምነት ፕሬዝደንት ትራምፕ በ2019 ውድቅ ካደረጉት ወዲህ ነው
ኢራን ጫና እያደረሰባት ከአሜሪካ ጋር የኑክሌር ድርድር አታደርግም ሲሉ የኢራኑ ፕሬዝደንት ፔዝሽኪያን ተናገሩ።
ኢራን ጫና ውስጥ ሆና ከአሜሪካ አትደራደርም ያሉት ፕሬዝደንት መሱድ ፔዝሽኪያን የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የፈለጉትን እንዲያደርጉ እንደነገሯቸው ሮይተርስ የኢራን ሚዲያዎችን ጠቅሶ ዘግቧል።
"የአሜሪካ ዛቻና ትዕዛዝ ተቀባይነት የለውም። ከአንተ ጋር መደራደር አልፈልግም። የፈለከውን ማድረግ ትችላለህ" ሲሉ ተናግረዋል ፔዝሽኪያን።
የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ካሚኒ ባለፈው ቅዳሜ ፕሬዝዳንት ትራምፕ የኑክሌር ድርድር ለማድረግ ለኢራን ደብዳቤ መጻፋቸውን ከገለጹ ከአንድ ቀን በኋላ ቴህራን በጫና አትደራደርም ብለዋል። ፕሬዝደንት ትራምፕ ከቴህራን ጋር ለመደራደር ያላቸውን ግልጽነት ቢያሳዩም ኢራን ከተቀረው አለም ለመለየትና የነዳጅ ኤክስፖርቷን ወደ ዜሮ ለማስገባት በመጀመሪያ የስልጣን ዘመናቸው ይጠቀሙት የነበረውን "ከፍተኛ ጫና" ተግባራዊ እያደረጉ ናቸው።
ፕሬዝደንት ትራምፕ ባለፈው ሳምንት ከፎክስ ኒውስ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ኢራን የኑክሌር ጦር መሳሪያ እንዳትጠቀም ለመከላከል ስምምነት ትፈርማለች ወይም ወታደራዊ እርምጃ ይከተላታል ሲሉ ተናግረዋል። ኢራን የኑክሌር ጦር መሳሪያ እንዳይኖራት ለረጅም ጊዜ ክልከላ ተጥሎባት ነበር። ይሁን እንጂ በከፍተኛ ፍጥነት ዩራኒየምን እያበለጸገች እንደሆነ እየተነገረ ነው።
ኢራን የኑክሌር ስራዋን ያፋጠነችው በ2015 ከስድስት ኃያላን ሀገራት ጋር የገባችውን የኑክሌር ስምምነት ፕሬዝደንት ትራምፕ በ2019 ውድቅ ካደረጉት ወዲህ ነው።