የኢራቅ የጤና ሚኒስቴር የቻይናው ክትባት ለአስቸኳይ ጊዜ አገልግሎት እንዲውል መጽደቁን አስታውቋል
የኢራቅ የጤ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ኢራቃ የቻይናን የኮቪድ-19 ክትባት ስርጭትን ለመግታት ለአስቸኳይ ጊዜ ለመጠቀም አጽድቃለች፡፡
የኢራቅ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ሴፍ አል-ባድር ለቻይና ዜና አገልግሎት ዥንዋ እንደገለጹት በቻይና ናሽናል ፋርማሱቲካል ግሩፕ (ሲኖፋርም) የተሰራው የቻይና ክትባት ከኤን.ቢ.ኤስ.ዲ ደረጃዎች ጋር የሚስማማ በመሆኑ የኢራቅ ግዛት በኢራቅ ውስጥ ጥቅም ላይ እንዲውል መፈዱን ገልጸዋል፡፡
ክትባቱን ለመቀበል ሁሉም የሎጅስቲክ ዝግጅቶች የተደረጉ ሲሆን ክትባቱን የሚወስዱ ቡድኖች ተለይተው መታየታቸውን ሚኒስቴሩ በሌላ መግለጫ አስታውቋል ፡፡
በቻይና ሁቤ ግዛት የቀሰቀሰው የኮሮና ቫይረስ መበላው አለም በማዳረስ የማህበራዊና ፖለቲካዊ ቀውስ አስከትሏል፤እያስከተለም ይገኛል፡፡
ለኮሮና ክትባት ለማግኘት በርካታ ሀገራት እሽቅድምድም ውስጥ በመግባት የተለያዩ ሀገራት ክትባት ማግኘታቸውን በተለያየ ጊዜ ገልጸዋል፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት ድሃ ሀገራት የክትባቱ ተጠቃሚ መሆን እንዳለባቸውም ገልጾ ነበር፡፡