በዛሬው ዕለት ብቻ 50 ሺ 237 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል
በመላው ዓለም በኮሮና የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ5 ነጥብ 5 ሚሊዬን አሻቅቧል
“ወርልዶ ሜትር” (https://www.worldometers.info/coronavirus/) የተሰኘው የወቅታዊ አሃዛዊ መረጃዎች ድረ ገጽ በመላው ዓለም በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር በአሁኑ ሰዓት 5 ሚሊዬን 542 ሺ 71 መድረሱን አመልክቷል፡፡
የጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ (https://coronavirus.jhu.edu/map.html)ደግሞ ቁጥሩን 5 ሚሊዬን 439 ሺ 559 ያደርገዋል፡፡
እንደ ወርልዶ ሜትር መረጃ ከሆነ በአሁኑ ሰዓት በቫይረሱ ተይዘው ሚገኙ ሰዎች ቁጥር 2 ሚሊዬን 873 ሺ 35 ነው፡፡ ከነዚህ መካከል 2 በመቶ ያህሉ ወይም 53 ሺ 272ቱ ጽኑ ህሙማን ናቸው፡፡
አጠቃላይ ያገገሙ እንዲሁም የሞቱ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 2 ሚሊዬን 669 ሺ 36 ነው፡፡ ከነዚህ መካከል 87 በመቶ ያህሉ ወይም 2 ሚሊዬን 321 ሺ 653ቱ አገግመው ከሆስፒታሎች ወጥተዋል፡፡ ቀሪዎቹ ደግሞ ህይወታቸው አልፏል፡፡
በመላው ዓለም የሚገኙ 213 ሃገራትንና ግዛቶችን ባዳረሰው በዚህ ቫይረስ ክፉኛ ከተጠቁ ሃገራት መካከል አሜሪካ ቀዳሚዋ ነች፡፡ በዛሬው ዕለት ብቻ 4 ሺ 793 በቫይረሱ መያዛቸው በተረጋገጠባት አሜሪካ ከ1 ነጥብ 6 ሚሊዬን በላይ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡ ዛሬ የሞቱትን 98 ሰዎች ጨምሮ በድምሩ የ99 ሺ 398 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡ 451 ሺ 801 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል፡፡
የወረርሽኙ አዲስ ማዕከል እየሆነች ነው በሚባልላት ብራዚል ደግሞ 365 ሺ 213 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ ዛሬ የሞቱትን 30 ሰዎች ጨምሮ በድምሩ 22 ሺ 746 ሰዎች ሞተዋል፡፡
ፕሬዝዳንት ቦልሶናሮ ወረርሽኙን ለመግታት የሚያስችሉ እርምጃዎችን አልወሰዱም፣ ቸልተኝነት ታይቶባቸዋል በሚል ከፍተኛ ተቃውሞ እና ትችል እየገጠማቸውም ይገኛል፡፡
8 ሺ 946 አዳዲስ ኬዞች ሪፖርት በተደረጉባት ሩሲያም የተያዘዉ ሰዎች ቁጥር 353 ሺ 427 ደርሷል፡፡ ዛሬ የሞቱትን 92 ሰዎች ጨምሮም የ3 ሺ 633 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡
ደቡብ አፍሪካ፣ግብጽ እና አልጄሪያን የመሳሰሉ ሃገራት ቀዳሚ የወረርሽኙ ተጠቂ በሆኑባት አፍሪካ ደግሞ ዛሬ ሪፖርት የተደረጉትን 1 ሺ 203 ኬዞች ጨምሮ 114 ሺ 859 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘው ይገኛሉ፡፡ ዛሬ የሞቱትን 39 ሰዎች ጨምሮም እስካሁን በድምሩ 3 ሺ 395 ሰዎች ሞተዋል፡፡ ያገገሙት ቁጥር ደግሞ 46 ሺ 406 ነው፡፡
ዛሬ 73 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን ሪፖርት ያደረገችው ኢትዮጵያም ባለፉት ሶስት ቀናት ብቻ 2 መቶ 22 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን በጤና ሚኒስቴሯ በኩል አስታውቃለች፡፡
በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥርም 6 መቶ 55 ደርሷል፡፡ የ5 ሰዎች ህይወት ያለፈም ሲሆን 1 መቶ 59 ታማሚዎች አገግመዋል፡፡