በፕሬዝዳት ቡሽ ላይ ጫማውን የወረወረው ሙንታዘር አል-ዛዲ ብስጭቱ ዛሬም እንዳለቀቀው ተናግሯል
በአሜሪካ የቀድመፐ ፕሬዝዳንት ጆርጅ ቡሽ ላይ ጫማውን የወረወረው ኢራቃዊ ጋዜጠኛ ተግሩን መፈጸሙ "አይጸጽተኝም" ማለቱ ተሰምቷል
ኢራቃዊው ጋዜጠኛ ሙንታዘር አል-ዛዲ በፈረንጆች 2003 የአሜሪካ ኢራቅን መውረር ተከትሎ በተፈጠረው ሙስናና ትርምስ የተሰማውን ቁጣ ለማሳየት በፕሬዝዳንት ጆርጅ ደብሊው ቡሽ ላይ ጫማውን በመወርወሩ ታዋቂነትን አግኝቷል።
በፕሬዝዳት ቡሽ ላይ ጫማውን የወረወረው ሙንታዘር አል-ዛዲ ብስጭቱ ዛሬም እንዳለቀቀው ከሰሞኑ መናሩ ተስመቷል።
ጋዜጠኛው ሙንታዘር አል-ዛዲ በፈረንጆቹ በ2008 በኢራቅ ባግዳድ ባግዳድ ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ በሚሰጥበት ወቅት ነበር ጫማውን ፕሬዝዳንት ጆርጅ ቡሽ ላይ የወረወረው።
ጫማ መወርወር በአረብ ባህል ትልቅ ስድብ ተደርጎ ይታያል።
አሜሪካ የቀድመፐ ፕሬዝዳንት ጆርጅ ቡሽ በወቅቱ የነበረውን የጫማ ውርወራ ክስተት አጣጥለውታል።
የአንድን ሀገር መሪ በመደብደብ ለስድስት ወራት በእስር ቤት የቆየው ዛዲ፤ ከእስር ከተፈታ በኋላ ወደ ሊባኖስ ቢሄድም በ2018 ሙስናን ለመዋጋት በኢራቅ ፓርላማ ለመወዳደር ተመለሷል።
ኢራቃዊው ጋዜጠኛ ሙንታዘር አል-ዛዲ ጫማውን በመወርወሩ ተጸጽቶ እንዳማያውቅም ለሮይተርስ ተናግሯል።