በአዲስ አበባ ለኢሬቻ በዓል ዝግ የሚደረጉ መንዶች የትኞቹ ናቸው?
ከአርብ መስከረም 25 እስከ ቅዳሜ በዓሉ እስኪጠናቀቅ የሚዘጉ የአዲስ አበባ መንገዶችን ቦሊስ ይፋ አድርጓል
የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል በአዲስ አበባ መስከረም 26 ቀን 2016 ይከበራል
በአዲስ አበባ የሚከበረው የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል ተከብሮ እስከሚጠናቀቅ የተወሰኑ መንገዶችን ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
መስከረም 26 ቀን 2016 ዓ.ም የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል በአዲስ አበባ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ይከበራል፡፡
በመሆኑም ከነገ ከዓርብ መስከረም 25 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ጀምሮ በዓሉ እስከሚጠናቅ
• ከቦሌ አየር መንገድ በሚሊኒዬም አዳራሽ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ወሎ ሰፈር አደባባይ
• ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ 22 ማዞሪያ
• ከ4ኪሎ በውጭ ጉዳይ ሚ/ር ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኮንሰን መስቀለኛ ወይም ወዳጅነት ፓርክ
• ከፒያሳ በቸርቸር ጎዳና ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቴዎድሮስ አደባባይ
• ከጦር ሃይሎች በለገሃር ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት
• ከጀሞ በትንባሆ ሞኖፖል ወደ ሜክሲኮ የሚወስደው መንገድ አፍሪካ ህብረት አደባባይ
• ከቄራ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ የሚሄደው መንገድ ቡልጋርያ ማዞሪያ
• በአዲሱ መንገድ ከቄራ በቂርቆስ ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ታቦት ማደሪያ
• ከሳሪስ ፣ በጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ጎተራ ማሳለጫ
• ከቦሌ ወደ ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን የሚወስደው መንገድ አትላስ ሆቴል አካባቢ
• ከአዋሬ ወደ ካሳንቺዝ የሚወስደው መንገድ ሴቶች አደባባይ
• ከልደታ በጌጃ ሰፈር ፣ ጤና ጥበቃ የሚወስደው መንገድ አብነት ፈረሰኛ ፖሊስ አካባቢ
• ከመርካቶ በጎማ ተራ ወደ አምስተኛ የሚወስደው መንገድ በርበሬ በረንዳ
• ከመርካቶ በራስ ቴአትር ወደ ጎማ ቁጠባ ተክለ ሃይማኖት አደባባይ
ከአርብ መስከረም 25 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ መንገዶቹ ለጊዜው ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑም ፖሎስ አስታውቋል።
በዓሉ በሚከበርበት ዙሪያ እና በአካባቢው በግራና በቀኝ ለረጅም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል፡፡
የዘንድሮ የኢሬቻ በዓል መስከረም 26 2019 ዓ.ም በአዲስ አበባ፤ መስከረም 27 2016 ዓ.ም ደግሞ በቢሾፍቱ ተከብረው ይውለሉ።