ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 352 ፍሊስጤማውያን ተገድለዋል ተባለ
የእስራኤል የአየር ድብደባ የቀጠለ ሲሆን፤ ዛሬ ጠዋት ብቻ 30 ፍሊስጤማውያን ተገድለዋል
ሃማስ ካገታቸው ውስጥ ሁለት የአሜሪካ ዜጎችን መልቀቁ ታውቋል
ከሁለት ሳምንት በፊት የፍልጤሙ ሃማስ በእስራኤል ላይ ጥቃት መሰንዘሩን ተከትሎ የተጀመረው ጦርነት አሁንም እንደቀጠለ ይገኛል።
በጦርነቱ እስራኤል በጋዛ የምትፈጽመውን የአየረ ድብደባ የቀጠለች ሲሆን፤ ሃማስም ወደ እስራኤል ሮኬቶችን መተኮሱን እንደቀጠለ ነው።
የእስራኤል ሃማስ ጦርነት አዳሩን ምን ተፈጠረ?
ሃማስ ካገታቸው ሰዎች መካከል ሁለት አሜረካውያንን ለቋል፤ ሌሎችንም ለመልቀቅ ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል።
እስራኤል በጋዛ የምታካሂደውን የአየር ድብደባ አዳሩንም የቀጠለች ሲሆን፤ ዛሬ ጠዋት ብቻ 30 ፍሊስጤማውያን መሞታቸውን ተዘግቧል።
በእስራኤል የአየር ድብደባ ባለፉት 24 ሰዓታት ብቻ 352 ፍሊስጤማውያን መገደላቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታውቋል።
በጦርነቱ እስካሁን የሞቱ ፍልጤማውያን ቁጥር 4 ሺህ 137 የደረሰ ሲሆን፤ ከእነዚህም 70 በመቶው ህጻት እና ሴቶች ናቸው።
የጋዛ የቤቶች ሚኒስቴር፤ በጋዛ ውስጥ የሚገኙ 30 በመቶ መኖሪያ ቤቶች በእስራኤል የአየር ድብደባ ወድመዋል ብሏል።
በኢራን የሚደገፈው ታጣቂ ቡድን በኢራቅ የሚገኘው የአሜሪካ ጦር በአስቸኳ ለቆ እንዲወጣ ያስጠነቀቀ ሲሆን፤ ይህ ካልሆነ እና አሜሪካ እስራኤልን መደገፏን ከቀጠለች ጥቃት እንደሚፈጽም ዝቷል።
አሜሪካ በግልጽ እና በቀጥታ ለእስራኤል ድጋፍ በማድረግ ላይ ስትሆን ኢራን በበኩሏ እስራኤል በጋዛ የጀመረችውን ጥቃት እንድታቆም አስጠንቅቃለች።