ፖለቲካ
አሜሪካ ሁለት "አይረን ዶም" የመከላከያ ስርዓቶችን ለእስራኤል ልትልክ መሆኑ ተገለጸ
መሳሪያዎቹ ወደ እስራኤል በሚቀጥሉት ቀናት ውስጥ ይዛወራሉ ተብሎ ይጠበቃል
ፕሬዝዳንት ባይደን በቀጣናው የአሜሪካን ወታደራዊ እንቅስቃሴ ከማሳደግ በተጨማሪ ለእስራኤል ጥይቶችን ለመላክ ቃል ገብተዋል
ፔንታጎን ከእስራኤል የገዛቸውን ሁለት "አይረን ዶም" የሚሳይል መከላከያ ስርዓቶችን መልሶ ለመላክ ማቀዱን የመንግስት ምንጮች ተናገሩ።
የአሜሪካ መከላከያ ሚንስቴር ለኮንግረስ አባላት በሰጠው ማብራሪያ የመከላከያ ስርዓቶችን ለእስራኤል መልሶ ለማከራየት ማቀዱን ተናግሯል።
መሳሪያዎቹ ወደ እስራኤል በሚቀጥሉት ቀናት ውስጥ ሊዘዋወሩ እንደሚችሉ ምንጮች ለሮይተርስ ተናግረዋል።
ፔንታጎን "አይረን ዶም"ን የጉዋምን ግዛት ከቻይና ሚሳይሎች ለመከላከል ሲያጤነው እና ሲሞክረው ቆይቷል።
ዋይት ሀውስ ከእስራኤል የሚቀርቡለትን ተጨማሪ የደህንነት ጥያቄዎች በተቻለ ፍጥነት እንደሚያሟላ ጠቁሟል።
ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በቀጣናው የአሜሪካን ወታደራዊ እንቅስቃሴ ከማሳደግ በተጨማሪ ለእስራኤል ጥይቶችን ለመላክ ቃል ገብተዋል።
"አይረን ዶም" ከሂዝቦላ ሮኬቶችና ከሀማስ ጥቃት ለመከላከል በአሜሪካ ድጋፍ በጎርጎሮሳዊያኑ 2011 ስራ ላይ ውሏል።
እስራኤል ባለፈው ዓመት በአንድ ሳምንት ከተወረወሩባት የፍልስጤም ሮኬቶች 97 በመቶ የሚሆነውን "አይረን ዶም" መመለሱን ተናግራለች።