እስራኤል ባለ 2ሺ ፓውንድ ክብደት ያለው የከባድ ቦምብ ጭነት ከአሜሪካ መረከቧን አስታወቀች
የኤምኬ-84 ቦምብ 2ሺ ፓውንድ ክብደት ያለው ሲሆን ወፍራም ኮንክሪቶችን ሰንጠቆ በመግባት ከባድ ፍንዳታ የሚያደርስ ነው
![](https://cdn.al-ain.com/images/2025/2/16/243-163758-img-20250216-152947-554_700x400.jpg)
እስራኤል ፕሬዝደንት ትራምፕ በቀድሞው ፕሬዝደንት ባይደን ተጥሎ የነበረውን የጦር መሳሪያ ኤክስፖርት እግድ ካነሱ በኋላ ኤምኬ-84 ቦምብ ጭነት መረከቧን ገልጻለች
እስራኤል ባለ 2ሺ ፓውንድ ክብደት ያለው የከባድ ቦምብ ጭነት ከአሜሪካ መረከቧን አስታወቀች።
እስራኤል ፕሬዝደንት ትራምፕ በቀድሞው ፕሬዝደንት ባይደን ተጥሎ የነበረውን የጦር መሳሪያ ኤክስፖርት እግድ ካነሱ በኋላ ኤምኬ-84 ቦምብ ጭነት መረከቧን ገልጻለች።
የኤምኬ-84 ቦምብ 2ሺ ፓውንድ ክብደት ያለው ሲሆን ወፍራም ኮንክሪቶችን ሰንጠቆ በመግባት ከባድ ፍንዳታ የሚያደርስ ነው።
ፕሬዝደንት ባይደን እነዚህን ቦምቦች ለእስራኤል እንዳይተላለፉ እግድ የጣሉት ብዙ ህዝብ በሚኖርባቸው የጋዛ አካባቢዎች ላይ ከባድ ጉዳት ያስከትላል በሚል ስጋት ነበር።
የባይደን አስተዳደር የፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን ሀማስ ጥቅምት 7፣2023 ድንበር ጥሶ በእስራኤል ላይ ጥቃት ከፈጸመ በኋላ በሺዎች የሚቆጠሩ 2ሺ ፓውንድ ክብደት ያላቸውን ቦምቦችን የላኩ ቢሆንም ዘግየት ብለው ቦምቦቹ እንዳይላኩ አድርገው ነበር።
"በትራምፕ አስተዳደር ፍቃድ ተለቀው ዛሬ ምሽት እስራኤል የደረሱት መሳሪያዎች ለእስራኤል አየር ኃይልና ለእስራኤል ጦር ወሳኝ ሀብት ናቸው፤ በእስራኤልና አሜሪካ መካከል ያለው ግንኙነትም የበለጠ ጠንካራ መሆኑን የሚያካይ ተጨማሪ መረጃ ነው" ሲሉ የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ ተናግረዋል።
ዋሽንግተን የጦር መሳሪያውን የላከችው ባለፈው ወር በእስራኤልና ሀማስ መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት የመቀጠሉ ጉዳይ ስጋት ከፈተጠረ ከቀናት በኋላ ነው።
ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ አሜሪካ ለእስራኤል በቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር የጦር መሳሪያ ድጋፍ አድርጋለች።