አሜሪካ ያሰናበተቻቸውን የኑክሌር ቦምብ ባለሙያዎች መልሳ ለመቅጠር እየፈለገች ነው ተባለ
ሰራተኞቹ የተሰናበቱት የአሜሪካው ፕሬዝደንት ትራምፕ ባለፈው ወር የፌደራል መንግስት ሰራተኞችን ለመቀነስ በያዙት እቅድ መሰረት ነው

ፕሬዝደንት ትራምፕ በሀገር ውስጥ በሁሉም ዘርፍና በውጭ ወጭ ለመቀነስ እየሰሩ ናቸው
አሜሪካ ያሰናበተቻቸውን የኑክሌር ቦምብ ባለሙያዎች መልሳ ለመቅጠር እየፈለገች ነው ተባለ።
የአሜሪካ መንግስት ባለፈው ሀሙስ ያሰናበታቸውን የኑክሌር ቦምቦ ደህንነት ባለሙያወች መልሶ ለመቅጠር እያፈላለጋቸው መሆኑን ተዘግቧል።
የብሔራዊ የኑክሌር ደህንነት አስተዳደር ሰራተኞች የስራ ስንብት ደብዳቤ ከደረሳቸው በመቶዎች ከሚቆጠሩት የኢነርጂ ወይም የኃይል ዲፓርትመንት ሰራተኞች ውስጥ ነበሩ። ቢቢሲ የአሜሪካውን ኤንቢሲ ኒውስ ጠቅሶ እንደዘገበው የተወሰኑት የኑክሌር ቦምብ ደህንነት ሰራተኞች ኢሜል አድራሻ በመሰረዙ በድጋሚ ለመቅጠር አግኝቶ አስቸጋሪ ሆኗል።
ሰራተኞቹ የተሰናበቱት የአሜሪካው ፕሬዝደንት ትራምፕ ባለፈው ወር የፌደራል መንግስት ሰራተኞችን ለመቀነስ በያዙት እቅድ መሰረት ነው። ባለፈው ሳምንት 10ሺ ገደማ የፌደራል መንግስት ሰራተኞች መቀነሳቸው ተገልጿል። ይህ ቁጥር ኃይት ሀውስ ባቀረበው ጥያቄ መሰረት በፈቃዳቸው ስራ ከለቀቁ 75 ሺ ሰራተኞች በተጨማሪ ነው።
ባለፈው ሀሙስ እለት የተሰናበቱት የኑክሌር ደህንነት ባለሙያዎች የሀገሪቱን የኑክሌር ጦር መሳሪያ ክምችት የሚቆጣጠሩ ነበሩ ተብሏል። የኑክሌር ጦር መሳሪያ በተገነባበት ጣቢያ የነበሩ ሰራተኞች ከተሰናበቱት ውስጥ ይገኙበታል።
ፕሬዝደንት ትራምፕ በሀገር ውስጥ በሁሉም ዘርፍና በውጭ ወጭ ለመቀነስ እየሰሩ ናቸው።ፕሬዝደንቱ ሰራተኞችን ለመቀነስ በአለም ቁጥር አንዱ ቢሊየነር አመሎን መስክ የሚመራውንና ሰራተኞቹን ወደ ፌደራል ተቋማት እያሰማራ ምርመራ የሚያደርገውን የመንግስት ውጤታማነት ዲፓርትመንትን(ዶጁ) ይጠቀማሉ።
ትራምፕ ባለፈው ሳምንት የኑክሌር ደህንነት ሰራተኞችን ጨምሮ የሙከራ ጊዜያቸው ያላለቀ ሁሉም ሰራተኞች እንዲሰናበቱ አቅጣጫ አስቀምጠው ነበር። ይህ ውሳኔ በመቶሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሰለባ ሊያደርግ ይችላል ተብሏል።