እስራኤል ከአሜሪካ ገዝታው የነበረውን የጦር አውሮፕላን ከአገልግሎት ውጪ አደረገች
ኤፍ 35ኤ ስያሜ ያለው አሜሪካ ሰራሽ የጦር አውሮፕላን ደህንነቱ አስተማማኝ ባለመሆኑ ነው ተብሏል
ይህ አውሮፕላን በቴክሳስ ለማረፍ ሲሞክር የመከስከስ አደጋ እንዳጋጠመው ተገልጿል
እስራኤል ከአሜሪካ ገዝታው የነበረውን የጦር አውሮፕላን ከአገልግሎት ውጪ አደረገች።
አሜሪካ ሰራሽ የሆነው ኤፍ-35ኤ የጦር አውሮፕላንን ከገዙት እና ከታጠቁት ሀገራት መካከል እስራኤል አንዷ ናት።
ይህ ዘመናዊ የጦር አውሮፕላን ባሳለፍነው ሳምንት በአሜሪካ ቴክሳስ የውጊያ ትዕይንት በማሳየት ላይ እያለ እክል እንደገጠመው ሮይተርስ ዘግቧል።
አውሮፕላኑ የቴክኒክ እክል ያጋጠመው መሬት ላይ ለማረፍ እየሞከረ እያለ የመከስከስ አደጋ ደርሶበታል ተብሏል።
አውሮፕላኑ ያጋጠመው አደጋ ተጨማሪ ምርመራ ያሚያስፈልገው እንደሆነ የእስራኤል አየር ሀይል እንደወሰነ በዘገባው ላይ ተጠቅሷል።
በዚህም ምክንያት የጦር አውሮፕላኑ ደህንነት እስኪረጋገጥ ድረስ ከእስራኤል አየር ሀይል ሲስተም ውስጥ እንዲወጣ ተደርጓልም ተብሏል።
በእስራኤል ጦር ስር ያለው ይህ የውጊያ አውሮፕላን በቴክሳስ የተፈጠረው አይነት አደጋ እንዳይከሰት ስጋት እንዳለበትም ተገልጿል።
ከ10 ወራት በላይ ያስቆጠረው የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ከሁለቱ ሀገራት በተጨማሪ በእጅ አዙር የሚሳተፉ ቁጥር እየጨመረ እንደሆነ ይገለጻል።
ኢራን ሰው አልባ የጦር አውሮፕላን ለሩሲያ እየሰጠች ነው የተባለ ሲሆን ዩክሬን እስራኤል የአየር ላይ ጥቃት ማምከኛ የጦር መሳሪያ እንድትረዳት ጠይቃለች።
ሩሲያ በበኩሏ እስራኤል ከዩክሬን የቀረበላትን ጥያቄ እንዳትቀበል ያስጠነቀቀች ሲሆን እስራኤልም በይፋ የዩክሬንን ጥያቄ ውድቅ ማድረጓ ይታወሳል።