ራሽፎርድ በማንቸስተር ዩናይትድ እስከ 2024 የሚያቆየውን አዲስ ኮንትራት ተፈራረመ
የ25 አመቱ እንግሊዛዊ የፊት መስመር ተጫዋች ከዩናይትድ አካዳሚ የተገኘ ነው
በአዲሱ ኮንትራት መሰረት ራሽፎርድ በሳምንት 250ሺህ ዩሮ እና ቦነስ የሚከፈለው ይሆናል
የማንቸስተር ዩናይትዱ አጥቂ ማርከስ ራሽፎርድ በክለቡ እስከ 2024 የሚያቆየውን ኮንትራት ተፈራረመ፡፡
በአዲሱ ኮንትራት መሰረት ራሽፎርድ በሳምንት 250ሺህ ዩሮ እና ቦነስ የሚከፈለው ሲሆን በፕሪምየር ሊጉ ካሉ እንግሊዛዊያን ተጨዋቾች ከፍተኛ ተከፋይ ያደርጓል ሲል ኢንዲፔንደንት ጋዜጣ ዘግቧል።
ከራሽፎርድ በተጨማሪ ዲዮጎ ዳሎት፣ ፍሬድ እና ሉክ ሻው በዩናይትድ ቤት ለመቆየት ኮንትራታቸው ያራዘሙ ተጨዋቾች ናቸው፡፡
የ25 አመቱ እንግሊዛዊ የፊት መስመር ተጫዋች ከዩናይትድ አካዳሚ የተገኘ ሲሆን በዚህ ወር የዓለም ዋንጫ ሩብ ፍጻሜ ላይ የደረሰው ብሔራዊ ቡድን አባል እንደነበር አይዘነጋም፡፡
የማንቸስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሃግ "እኛ ማሻሻል እንፈልጋለን፣ እነዚያን ተጫዋቾች መደገፍ እንፈልጋለን እና የእቅዳችን አካል ሆነው እንዲቀጥሉ እንፈልጋለን። ለወደፊት ቡድን መገንባት እንፈልጋለን፣ ስለዚህ ረዘም ላለ አመታት ተጫዋቾቹ የዚህ አካል መሆን አለባቸው" ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በደረጃ ሰንጠረዡ 5ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው የኤሪክ ቴን ሃግ ቡድን ማክሰኞ እለት ከተጠናቀቀው የዓለም ዋንጫ እረፍት በኋላ ወደ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ የሚመለስ ይሆናል፡፡