ፖለቲካ
እስራኤል በጋዛ እና በሊባኖስ ነጭ ፎስፈረስ ተጠቅማለች የሚል ክስ ቀረበባት
ሂውማን ራይትስዎች እንዲህ አይነት መሳሪያዎችን መጠቀም ንጹሃንን ለአጭር እና ለረጅም ጊዜ ጉዳት ያጋልጣል ብሏል
ሀማስ የእስራኤልን ድንበር በመጣስ ያልተጠበቀ ጥቃት ማድረሱን ተከትሎ እስራኤል በጋዛ በሚገኙ የሀማስ ይዞታዎች ላይ መጠነሰፊ የአጸፋ ጥቃት እየፈጸመች ትገኛለች
እስራኤል በጋዛ እና በሊባኖስ ባደረሰችው ጥቃት ጥቅም ላይ እንዳይውል የተከለከለውን ነጭ ፎስፈረስ ተጠቅማለች ሲል ሂውማን ራይትዎች ከሷል።
ሂውማን ራይትስዎች እንዲህ አይነት መሳሪያዎችን መጠቀም ንጹሃንን ለአጭር እና ለረጅም ጊዜ ጉዳት ያጋልጣል ብሏል።
በቀረበበት ክስ ላይ ምላሽ እንዲሰጥ የተጠየቀው የእስራኤል ጦር "ነጭ ፎስፈረስ የያዙ መሳሪያዎች በጋዛ ጥቅም ላይ መዋላቸውን እንደማያውቅ" የገለጸ ሲሆን ስለሊባኖሱ ጥቃት ግን መልስ አልሰጠም።
ሀማስ የእስራኤልን ድንበር በመጣስ ያልተጠበቀ ጥቃት ማድረሱን ተከትሎ እስራኤል በጋዛ በሚገኙ የሀማስ ይዞታዎች ላይ መጠነሰፊ የአጸፋ ጥቃት እየፈጸመች ትገኛለች።
ጋዛን የከበበችው እስራኤል በሰሜን ጋዛ የሚኖሩ 1.1 ሚሊዮን ነዎሪዎች አካባቢያቸውን እንዲለቁ የ24 ሰአታት ማስጠንቀቂያ ሰጥታለች።
ይህን ተከትሎም ነዋሪዎች ከሰሜን ጋዛ እየወጡ ናቸው።
አለምአቀፍ የመብት ተቋማት እና ተመድ እስራኤል ነዋሪዎች እንዲወጡ ያቀረበችውን ማስጠንቀቂያ ሰብአዊ ቀውስ ይፈጥራል በማለት ተቃውመውታል።