እስራኤል በጋዛ ላይ ያዘነበችው ቦምብ አሜሪካ በአይኤአይኤስ ላይ ካወረደችው ይበልጣል ተብሏል
እስራኤል በጋዛ ላይ ስድስት ሺህ ቦምብ ማዝነቧን አስታወቀች።
ከአንድ ሳምንት በፊት የፍልስጤሙ ሀማስ በእስራኤል ላይ ድንገተኛ ጥቃት መክፈቱን ተከትሎ በአካባቢው ጦርነት ተቀስቅሷል።
እስካሁን በቀጠለው ጦርነት ከሁለቱም ወገን የሟቾች ቁጥር ከሶስት ሺህ በላይ የደረሰ ሲሆን በየደቂቃው ሰዎች ህይወታቸው እያለፈ ይገኛል።
እስራኤል በሀማስ ላይ እየወሰደችው ያለውን እርምጃ ቡድኑ ከምድረ ገጽ እስከሚጠፋ ዘመቻዬን እንቀጥላለሁ ስትል አስታውቃለች።
የሀገሪቱ ጦር እንሳስታወቀው በጋዛ እና በሌሎች የፍልስጤም መኖሪያ አካባቢዎች ላይ ስድስት ሺህ ቦምብ ማዝነቡን ገልጿል።
እስራኤል ወደ ፍልስጤም መንደሮች ያዘነበቻቸው ቦምቦች አሜሪካ ለአመታት በአይኤስኤይኤስ ላይ ከጣለችውም ይበልጣል ተብሏል።
በሺዎች የሚቆጠሩ የሀማስ ተዋጊዎች መገደላቸውን የሚገልጸው የእስራኤል ጦር ወታደራዊ መሰረተ ልማቶች፣ የታጣቂ ሙኖሪያዎች እና ቢሮዎች የጥቃቱ ኢላማ እንደሆኑ ተገልጿል።
ከ2 ሚሊዮን በላይ ፍልስጤማዊያን የሚኖሩበት ጋዛ ከባድ ጉዳት የደረሰበት ሲሆን መሰረታዊ አገልግሎቶች ሙሉ ለሙሉ ተቋርጠዋልም ተብሏል።
ባለፉት ሰባት ቀናት በቀጠለው ጦርነት 1ሺህ 400 ፍልስጤማዊያን እንደተገደሉም ተገልጿል።