እስራኤል ስምምነት ከተደረሰ 15ዐሺ ተፈናቃዮች ወደ ሰሜናዊ ጋዛ እንዲመለሱ እፈቅዳለሁ አለች
ባለስልጣናቱ እንገለጹት ከሆነ እስራኤል ሀማስ ይስማማል የሚል ግምገማ የላትም
ሀማስ በአደራዳሪዎቹ ግብጽ እና ኳታር በኩል የቀረበለት የተኩስ አቁም የውሳኔ ሀሳብ ውድቅ ማድረጉ ይታወሳል
እስራኤል ስምምነት ከተደረሰ 15ዐሺ ተፈናቃዮች ወደ ሰሜናዊ ጋዛ እንዲመለሱ እፈቅዳለሁ አለች።
እስራኤል በግብጽ በተካሄደው የተኩስ አቁም ድርድር ላይ ተፈናቃዮች ወደ ሰሜናዊ ጋዛ እንዲመለሱ እንደምትፈቅድ የእስራኤል ባለስልጣናት በዛሬው እለት ተናግረዋል።
ነገርግን እስራኤል እስላማዊው ቡድን ሀማስ ስምምነት ላይ መድረስ ይፈልጋል ብላ አታምንም ብለዋል ባለስልጣኑ።
ድርድሩን በቅርብ የሚከታተሉ ሁለት ባለስልጣናት ለሮይተርስ እንደተናገሩት እስራኤል አሜሪካ ባቀረበችው የተኩስ አቁም የውሳኔ ሀሳብ ላይ ያለምንም ፍተሻ 150ሺ ተፈናቃዮች ወደ ሰሜናዊ ጌዛ እንዲመለሱ ተስማምታለች።
እነዚህ ባለስልጣናት እንዳሉት እስራኤል በምላሹ ሀማስ በህይወት ያሉትን የህጻናት፣ በእድሜ የገፉ እና የታመሙ ታጋቾችን ዝርዝር እንዲሰጣት ትፈልጋለች።
ሀማስ ባለፈው ማክሰኞ በአደራዳሪዎቹ ግብጽ እና ኳታር በኩል የቀረበለት የተኩስ አቁም የውሳኔ ሀሳብ የየትኛውንም የፍልስጤም ታጣቂ ቡድን ፍላጎት አያሟላም፤ ነገርግን ምላሽ ለመስጠት በዝርዝር እየዋለሁ ብሎ ነበር።
ባለስልጣናቱ እንገለጹት ከሆነ እስራኤል ሀማስ ይስማማል የሚል ግምገማ የላትም።
ግብጽ፣ ኳታር እና አሜሪካ፤ እስራኤል እና ሀማስ ልዩነቶቻቸውን አጥብበው የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ እንዲደርሱ ጥረት ቢያደርጉም፣ እንዳቸው ያበረቁትን ቅድመ ሁኔታ ሌላኛቸው ውድቅ እያደረጉ ቀጥለዋል።
ሀማስ እስራኤል ወረራዋን እንድታቆም፣ ጋዛን ለቃ እንድትወጣ እና ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ይፈልጋል።
እስራኤል በአንጻሩ የጋዛን የደህንነት ቁጥጥር በስሯ ሆኖ እንዲቀጥል ትፈልጋለች።
ባለፈው ጥቅምት ወር ሀማስ ድንበር ጥሶ በእስራኤል ላይ የፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ የተቀሰቀሰው ጦርነት ስድስት ወር አልፎታል።
የጋዛ የጤና ባለስልጣናት እንደሚሉት ከሆነ በእስራኤል ጥቃት እስካሁን ከ32ሺ በላይ ፍልስጤማውያን ተገድለዋል።